ስፖርት፤ ሕዳር 6 ቀን 2008 ዓ,ም
ሰኞ፣ ኅዳር 6 2008በስፔን ኢንተርናሽናል ሀገር አቆዋራጭ አትሌቲክስ ውድድር አትሌት ኢማን መርጊያ 2:30:17 በመግባ ት አሸናፊ ሆነዋል። አትሌት ኢማን መርጊያ ፤ ይህን ውድድር በተከታተይ ሲያሸንፍ የአሁኑ ለአምስትኛ ጊዜ ነው። ዩጋንዳዊው ቲሞቲ ቶሮቲች፤ ሁለት ሰዓት ከሰለሳ ደቂቃ ከሀመሳ አምስት ሰከንድ ሁለተኛ የባህሬኑ አያሌው አወቀ ሶስትኛ በመሆን ውድድሩን ጨርስዋል።
በተመሳሳይ በሴቶች ውድድር እትዮጵያዊትዋ በላይነሽ ኦ ልጂራ አሸነፊ ሆናለች። በላይነሽ ያለፈውም ዓመት የርቀቱ አሸናፊ እንደነበረች ይታወቃል። በጃፓን ሳይታማ ማራቶን ውድድር አትሌት አፀደ ባይሳ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ 44 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆናለች። የጃፓንዋ ኮርያ ዮሺዳ 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ 43 ሰከንድ ሁለተኛ ስትሆን ኬንያዊትዋ ርብካ ቺሰር 2 ሰዓትከ 29 ደቄቃ 11 ሰከንድ ሶስትኛ በመሆን ውድድርዋን አጠናቃለች። ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን የራሺያዉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኦሎምፒክ ጨዋታዋችን ጨምሮ ከማነኛውም ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማገዱን አስታውቆዋል ። ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን ማህበር ምክር ቤት 22 ለ 1 በሆነ ድምፅ ውሳኔውን ያሳለፍው ዓለም አቀፍ የፀረ አበረታች መድሐኒት ገለልተኛ አጣሪ ወገን ያውጣውን ዘገባ ተከትሎ ነው።
የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ ሁለት የኮንጎን እግር ኳስ ማህበር ባለስልጣናትን ከሀላፊነት ማገዱን አስታውቆዋል። ሁለቱ የኮንጎ እግር ኳስ ባለስልጣናት ምክትል ፕሬዝዳንት ጂን ጋይ ብላሲ ማዮላስ እና፡ ጠቅላላ ፀሐፌው ባዲጄ ሞንቦ ዋንቲቲ የስድስት ወር እገዳ ቅጣት ነው የተጣለባቸው። ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን እና አስራ ሁለት ሀገሮች የሚገኝበትን የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ሻንፒዮና ድልድል ይፈ ሲወጣ አስተናጋጅዋ ኢትዮጵያ በምድብ ሀ ርዋንዳን የምታስተናግድበት ጎረቤታሞቹ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ለመጀመሪያ ጊዜ በምድብ ሐ እርስ ብርስ የሚፋለሙበት ሻንፔዮኑ ኬንያ የአስራ ሶስት ጊዜ አሸናፊውን ዩጋንዳን በምድብ ለ የሚገጥምበት ሆንዋል። በውድድሩ ተካፋይ ያልሆነችው ኤርትራ ጥያቄዬን ኢትዮጵያ ውድቅ አደረገችብኝ ስትል እትዮጵያ ደግሞ በበኩልዋ አላደረኩም ስትል ማስተባበልዋ ተዘግቧል። የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ማህበር ጠቅላላ ፀሀፊ ኒኮላስ ሞሶኒ የአካባቢው እግር ኳስ አካል ኢትዮጵያ የኤርትራን ቡድን ያለመፍቀድ አቋሟን ማክበር አለበት ማለታቸውን ጠቅሶ አሶሴትድ ፕሪስ ዘግቦዋል ።
«ኤርትራ የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪቃ ማህበርን ለመፈትን እንጂ በርግጥ ከወጣ የማይመለስ የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አይመስለኝም» ያለው ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ነው። ሀንጋሪ ኖርዌይን 2ለ1 በማሸነፍ ለ2016 ዓ,ም የአውሮፓ ዋንጫ ጫዋታ ከረጅም ዓመታ በኋላ ማለፉን አረጋገጠ። የቦሲንያ ሂርዞጎቢንያ እና የሪፐብሊክ አየር ላንድ ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ ማታ በደብሊን ይካሂዳል።
ነገ ዮክሬይን ከስሎቫኪያ እና ሲውዲን ከዴንማርክ ይጫወታሉ። በብራዚል በተከሂደው የብረዚል ግራንድ ፕርክስ የመኪና ውድድር ጀርመናዊው ኒኮ ሮዝብርግ እሸናፊ ሆነ። የማርሰዲስ የበላይነት በታየበት በብራዚሉ ውድድር ሉዊስ ሀሚልተን ሁለተኛ ሲቫስትያን ቪትል ሶስተኛ በመሆን አሸናፍፊ ሆነዋል።
ሃና ደምሴ
አዜብ ታደሰ