1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት፤ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2010

በእግርኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የራሺያው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በ12 የራሽያ ስታድየሞች ከጀመረ ዛሪ 5ኛ ቀኑን ይይዟል ። ከምድብ «ሸ» ቤልጅየም ከፓናማ የአፍሪቃዊትዋ ሀገር ቱኒዝያ፤ ከኢንግላንድ ጋር አንደዚሁም፤ በምድብ «ረ» ሲውዲን፤ ከደቡብ ኮርያ ጋር ይጫወታሉ።

https://p.dw.com/p/2zm7g
Fußball WM 2018 Gruppe F Deutschland - Mexiko
ምስል Reuters/A. Schmidt

የዓለም የእግር ኳስ ግጥምያ እና የሜዳ ቴኒስ

እግር ኳስ 

እስከትላንት በታዩት 13 ጨዋታዎች በተወሰኑ ምድቦች አስቀድሞ የሚያልፍውን ጠንካራ ቡድን መለይት አያስቸግርም። አስተናጋጅዋ ራሽያ በመክፈቻው ጨዋታ ሳውድ አረቢያን 5 ለዚሮ በመርታት በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ብዙ ጎል በማግባት ከጣልያን ቀጥላ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች። በ5ቱ ቀናት ጨዋታ 25 ጎሎች ከመረብ በማረፍ ጎል ተብለው ተመዝግበዋል።  ራሺያ፤ ኡራጋይ፤ ኢራን፤ ፍርንሳይ፤ ዲንማርክ፤ ክሮሺያ፤ ሰርቢያ እና ሚክሲኮ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያሸነፍ ሀገሮች ሆነዋል። 6ት ሀገራት ነጥብ ጥለው ወተዋል። የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያረጉት 3 የአፍሪቃ ሀግሮች በመጀመሪያው ጨዋታ ድል አልቀናቸውም። 

Fußball WM 2018 Gruppe F Deutschland - Mexiko
ምስል Reuters/A. Schmidt


የሜዳ ቲንስ
በኒዘርላንር በተካሄደው የወንዶች የነጠላ ሜዳ ቲንስ ውድድር፤ ፈረንሳዊው ሪቻርድ ጋስኮት የሀገሩን ልጅ የ31 ዓመት ይን ጀርሚ ቻርድን 6ለ4 7ለ6 እና 6 ለ 2 በአጠቃላይ 2 ለ1 አሽንፎዋል። በተመሳሳይ  በእንጊሊዝ  በርንግሀም ከተማ  በተካሄደ የሴቶች የነጠላ የሚዳቲንስ  ውድድር አንግሊዛዊትዋ ጆዋና ኮንታ በአውስትራልያዊትዋ ተጋጣሚ  2ለ1 ተሸንፋለች። ከዛሪ ጀምሮ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የራሺያ ከተሞች የከተሙት የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ቡድኖች የምድብ ቀሪ 36 ጨዋታዎችን ያደርጋሉ። ከዚህ በተጨማሪ  በያዝነው ሳምንት 3 የአውሮጳ ከተሞች የአንድ ሳምንት የሚዳ ቴንስ ውድድራቸውን ዛሬ ጀምረዋል። ሀገሮቹ እንጊሊዝ ጀርመን አና ስፒን ናቸው። በሚዳቲንስ አፍቃሪዎች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የዊምብልደን የሜዳ ቲንስ በመጭዉ ወር ይጀመራል።

ATP 250 Stuttgart Open | Roger Federer, Turniersieger
ምስል Reuters/R. Orlowski


ሃና ደምሴ  
አዜብ ታደሰ