ስፖርት፤ ታህሳስ 1 ቀን፤ 2011 ዓ.ም
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊቷ የእግር ኳስ ጨዋታ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ከስድስት ወር በኋላ ለሚካሔደው ለስምንተኛው የዓለም የሴቶች ዋንጫ ዝግጁ መሆኗን ለ«DW» ተናግራለች። ሊዲያ በፈረንሳይ የሚካሔደውን የዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ከተመረጡ ሦስት አፍሪቃውያን መካከል አንዷ ናት። ከዚህ በተጨማሪ በትናንትናው ዕለት በቻይናዋ በተካሔደ የማራቶን ውድድር በሴቶች ጎራ ኢትዮጵያውያኑ ትዕግስት ግርማ እና ዝናሽ ደበበ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በወንዶቹ ጎራ የኬንያው ሞሮኳዊው ሞሐመድ ዛይኒ አሸናፊ ሆኗል። ኢትዮጵያውያኑ ጋዲሳ ሹሜ እና ባለው ደረሰ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዕለቱ የስፖርት መሰናዶ ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች በተጨማሪ በሳምንቱ መገባደጃ የተካሔዱ የተለያዩ ጨዋታዎችን ይዳስሳል።
ሐይማኖት ጥሩነሕ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ