ስፖርት፤ ኅዳር 24፤ 2011 ዓ.ም
ሰኞ፣ ኅዳር 24 2011አትሌቲክስ
ሲንዥን በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ200 በላይ ተውዳዳሪዋች ውድድር በማጭበርበራቸው ታግደዋል። ቅዳሜ በተካሂደው የ 21 ኪሎ ሜትር ውድድር በተከለለው መንገድ መሮጥ ሲገባቸው በጫካ አቁዋርጠው ውስድድሩን የጨረሱ 258 ተውዳዳሪዋችን አና ሦስት ለሰው የሚሮጡ ተወዳዳሪዋችን መያዙን የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቲ አስታውቋል። በቻይና ከአሁን በኋላ በሚደረጉ የማራቶን ውድድሮች ፊትን የሚያስታውሱ እና የሚመዘግቡ መሳሪያዎች መጠቀም እንደሚጀመር ተገልጿል።
የሴቶች እግር ኳስ
በጋና አክራ ቅዳሜ ዕለት የተጠናቀቀው የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዋንጫ በናይጀሪያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ። የናይጀሪያ የሴቶች ቡድን እና የደቡብ አፍሪካ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ያደረጉት ጨዋታ መደበኛ ሰዓት እና ተጭማሪ 30 ደቂቃ ያለምንም ግብ በማለቁ አሽናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት የናይጀሪያ ቡድን 4 ለ3 ረቷል።
በሌላ በኩል ትናንት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በተስተናግዱት የደርቢ ጨዋታ ቸልሲ ፍልሀምን፤ አርስናል ቶትንሀምን ሲረቱ ሊቨርፑል ባለቀ ሰዓት በ96ኛው ደቂቃ ኤቨርተንን አሸንፏል።
ቦክስ
ቅዳሜ በተደረገ የዓለም ከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፕዮን ታይሰን ፉሪ አና ዲያንቲ ዋይልደር በ12ኛው ዙር በሚያስገርም ሁኒታ አቻ ተለያይተዋል። ከለንደን ሃና ደምሴ አጠናቅራዋለች። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ