ስፖርት
ሰኞ፣ ነሐሴ 1 2009ማስታወቂያ
ለንደን ብሪታንያ በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ እስከዛሬ በአንድ የወርቅ እና በሁለት የብር ሜዳልያ በሜዳልያው ሰንጠረዥ ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥላ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች። አትሌት ሞ ፋራህ በድል ዩዜይን ቦልት በሽንፈት ከአትሌቲክስ በጡረታ መሰናበታቸው እና የኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና የ10 ሺህ ሜትር ድንቅ አጨራረስ የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አስገራሚ ክስተቶች ተብለዋል። የዓለም አትሌቲክ ሻምፕዮና ዝርዝር ዘገባ ፣የዓለማችን ውድ ክፍያ የተፈጸመበት የብራዚላዊው እውቅ የእግር ኳስ ተጫዋች የኔይማር ከባርሴሎና የእግር ኳስ ክለብ ወደ ፓሪ ሳን ዠርማ ዝውውር፣የአውሮጳ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ እና ሌሎችም ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አበይት ስፖርታዊ ክንውኖች በስፖርት ዝግጅታችን ተካተዋል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ