1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት ፤ ነሐሴ 13፤ 2011 ዓ.ም

ሰኞ፣ ነሐሴ 13 2011

«CECAFA» የሴካፋ ከአስራ አምስት ዓመት በታች «ቻሌንጅ ካፕ» ለመጀመርያ ጊዜ መካሄድ በኤርትራ አስተናጋጅነት ጀምሮአል። ከባለፈዉ ሳምንት አርብ ነሐሴ 10 ፤ 2011 ዓም አንስቶ በአስመራ ከተማ መካሄድ የጀመረዉ ይህ የእግርኳስ ግጥምያ  በመክፈቻዉ ሥነስርዓት አስተናጋጅዋ ኤርትራ ብሎም ኢትዮጵያም ሽንፈትን ተጋፍጠዋል።

https://p.dw.com/p/3O7TT
Fußball Bundesliga Bayer Leverkusen - SC Paderborn
ምስል picture-alliance/dpa/R. Vennenbernd

በጀርመን ቡንደስሊጋ ሻንፒዮኑ ባየርን ሙኒክ ቀዳሚ ነጥብን ጥሎአል

 

«CECAFA» የሴካፋ ከአስራ አምስት ዓመት በታች «ቻሌንጅ ካፕ» ለመጀመርያ ጊዜ መካሄድ በኤርትራ አስተናጋጅነት ጀምሮአል። ከባለፈዉ ሳምንት አርብ ነሐሴ 10 ፤ 2011 ዓም አንስቶ በአስመራ ከተማ መካሄድ የጀመረዉ ይህ የእግርኳስ ግጥምያ  በመክፈቻዉ ሥነስርዓት አስተናጋጅዋ ኤርትራ ብሎም ኢትዮጵያም ሽንፈትን ተጋፍጠዋል። አስራ አንድ ብሔራዊ ቡድኖች በሦስት ምድብ ተከፍለዉ እስከ ነሐሴ 26፤ 2011 ዓ.ም ድረስ በሚያካሂዱት የሴካፋ ዋንጫ ግጥምያ በመክፈቻዉ ጨዋታ የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ አቻዉ ሁለት ለአንድ በሆነ ዉጤት ተሸንፎአል። ቅዳሜ እለት በተካሄደዉ ግጥምያ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚዉ በሆነዉ በዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ሦስት ለባዶ ተሸንፎአል። ኬንያ እና ብሩንዲም ተጋጣሚዎቻቸዉን አሸንፈዋል።  ተተኪ ተጫዋቾችን ለክለቦችም ሆነ ለብሔራዊ ቡድን ለማፋራት እንዲያስችል የተመሰረተዉ የሴካፋ ከአስራ አምስት ዓመት በታች የዋንጫ ግጥምያ መጀመር እንደ አንድ መልካም ርምጃም ተወስዶአል። ኢትዮጵያም ለዚሁ አዲስ ብሔራዊ ቡድን ማቋቋም እና አዲስ አሰልጣኝ በመሾም ነበር በአጭር ጊዜ ዉስጥ ዝግጅት አድርጋ ቡድኗን ለግጥምያ ዉድድሩ ወደ አስመራ የላከችዉ። 
በሌላ የስፖርት ዜና፤ ባሳለፍነዉ ሳምንት በጀርመን ቡንደስ ሊጋ በተጀመረዉ አዲስ የግጥምያ ዘመን የቡንደስ ሊጋዉ ሻንፒዮን ባየርን ሙኒክ በቀዳሚ ጨዋታ ነጥብን ሲጥል፤ ቦርሲያ ዶትሙንድ ደግሞ በግብ ተንበሽብሾአል። ኸርታ በርሊንን የገጠመዉ ባየር ሙኒክ በመጀመርያዉ ጨዋታ ሁለት ለሁለት በሆነ አቻ ዉጤት ተለያይቶአል። ቦርሲያ ዶትሙንድ ደሞ ሆክስ በርግን አምስት ለአንድ በሆነ ሰፊ ዉጤት ረቶታል። 

CECAFA Fussball-Cup
ምስል EBRAHIM HAMID/AFP/Getty Images

ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ