1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት ነሐሴ 30 ቀን 2008 ዓ.ም

ሰኞ፣ ነሐሴ 30 2008

በሳምንቱ መጨረሻ ለአፍሪቃ ዋንጫ ከተደረጉ ዉድድሮች መካከል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዋሳ ላይ ዉጤት ቀንቶታል። የጀርመን ብሔራዊ ቡድንም በዓለም ዋንጫ ቀዳሚ ጨዋታዉ ድልን አስመዝግቦ ተመልሶአል።

https://p.dw.com/p/1Jw1T
Fussball WM-Qualifikation Slowakei - England
ምስል picture alliance/empics/N. Potts

ስፖርት ነሐሴ 30 ቀን 2008 ዓ.ም



በሬዮ ኦሎምፒክ ከመቼዉም ጊዜ ይበልጥ ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገበዉ የኬንያ ኦሎምፒክ ቡድን ከሪዮ መልስ ከፍተኛ ዉጥግብ ላይ መገኘቱ የሚሉትና ሌሎችም ዓለም አቀፋዊ ትኩስ ስፖርታዊ ዜናዎች በዛሬዉ የስፖርት ዘገባ ላይ ተካተዋል።
በጋቦን አስተናጋጅነት በመጭዉ ዓመት የሚከናወነዉ የ 2017 ቱ የአፍሪቃ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአፍሪቃ መዲናዎች ተከናዉነዋል። በአዲስu የአዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሲሸልስ ብሔራዊ ቡድንን ያስተናገደዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን « ዋልያዎች » ተጋጣምያቸዉን ሁለት ለአንድ በሆነ ዉጤት ረተዋል። ምንም እንኳ ሲሸልሶች ጎል በማስቆጠሩ ቀዳሚነቱን ቦታ ቢወስዱም ጌታነህ ከበደ ለዋሊያዎቹ ቀዳሚ ያደረገችዉን ኳስ ከመረብ ሲያገናኝ ፤ ግቧ ለጌታነህ በአፍሪቃ ዋንጫ ማጣርያ ያስቆጠራት ስድስተና ግብ ሆና ተመዝግባለች። ከረፍት መልስ ኢትዮጵያ ያገኘችዉን የቅጣት ምት ሰላዲን ሰዒድ በመምታት ኢትዮPEያን አሸናፊነት ያበቃችዉን ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮአል። የቅዳሜዉን ጨዋታ ዉጤት ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምድቧ ስምንት ነጥብ በመያዝ አልጀርያን ተከትላ በሁለተኝነት ደረጃ ተቀምጣለች። ሲሸልስና ሌሴቶም አራትና ሦስት ነጥቦችን በመያዝ የሦስተኛና የአራተኛ ደረጃነትን ይዘዉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ ጋቦን ለማቅናትም ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይላታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሌሎች የአፍሪቃ ከተሞች በተካሄዱት የማጣርያ ግጥምያዎች መካከልም ካሜሩን ጋንብያን ሴኔጋል ሁለት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ሲያሸንፉ አይቮሪኮስት ከሴራሊዮን ጋና ከሩዋንዳ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ዉጤት ተለያይተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በዓለም ዙርያ የተካሄዱትን አበይት የስፖርት ጥንቅሮች ዘገባ የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

Fussball WM-Qualifikation Norwegen - Deutschland
ምስል picture alliance/dpa/F. Gambarini


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ