1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት፤ ጥቅምት 19፤  2011 ዓ.ም

ሰኞ፣ ጥቅምት 19 2011

በስፔን በጀርመን በስሎቫንያና በአየርላንድ በተካሄዱ የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ዉድድሮች ከቫሌንስያዉ ዉድድር በስተቀር ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በየአቅጣጫዉ በሁለቱም ፆታዎች በማሸነፍ ድርብ ድል ተጎናጽፈዋል።

https://p.dw.com/p/37LvP
Trauer nach Hubschrauberabsturz am King Power Stadion in Leicester
ምስል Getty Images/AFP/P. Ellis

ስፖርት፣ ጥቅምት 19 ቀን፣ 2011 ዓም

37 ኛዉ የፍራንክፈርት የጎዳና ላይ ዉድድር ትናንት በጀርመን ሲካሄድ በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በዉድድሩ ከሁለት ሰዓት አስር ደቂቃ በታች ሰዓት ያላቸዉ 14 አትሌቶች እና ሁለት ሰዓት ከ 25 ደቂቃ በታች ሰዓት ያላቸዉ ሴት አትሌቶች ተካፍለዉበታል። አስቀድሞ በኢትዮጵያዊዉ አትሌት ከልክሌ ገዛኸኝ እና በኬንያዊዉ አትሌት ማርቲን ኮስካይ መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይካሄዳል ተብሎ እንደተጠበቀ ሁሉ ሁለቱ አትሌቶች የተቀዳደሙት በአራት ሰከንድ ብቻ ነዉ። ከልክሌ ገዛኸን ሁለት ሰዓት ከዜሮ ዘጠኝ ደቂቃ ከ ሰላሳ ሰባት ሰከንድ ቀዳሚ ሲሆን ማርቲን ኩስኪ ሁለት ሰዓት ከዜሮ ስድስት ደቂቃ ከአርባ አንድ ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆንዋል። ቀሪዉ ከሦስተኛ እስከ ስድስተና ያለዉ ደረጃ በኬንያዉያን አትሌቶች ተይዞአል። በሳምንቱ መጨረሻ የተካሄዱ ሌሎች የአትሌክስ ዉድድሮችን ጨምሮ የኢንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ግጥሚያዎች በሳምንታዊዉ የስፖርት ጥንቅር ተካተዋል። ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ