1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2006

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፤ በሶቺ ፣ ሩሲያ ለሚጀመረው የክረምት ኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር ዝግጅቱ እንደቀጠለ ሲሆን ፤ የተቃውሞ ሰልፍ ቢፈቀድም የፀጥታው ቁጥጥር ጠበቅ ያለ እንደሚሆን ተገልጧል። በመጪው ሰኔ ዓለም በጉጉት የሚጠባበቀው የዓለም የአግር

https://p.dw.com/p/1Am5V
ምስል picture-alliance/Pressefoto UL

ኳስ ዋንጫ ዝግጅት የተሣካ እንደሚሆን የ FIFA ፕሬዚዳንት ዜፕ ብላተር ገለጡ። ብላተር ዛሬ እንዳሉት ብራዚል ውስጥ በ 12 የአግር ኳስ ስታዲየሞች ዝግጅቱ በተሟላ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው። በጀርመን አሁን በተያዘው የክረምት ዕረፍት ሳቢያ በአንደኛ ምድብ የአግር ኳስ ክለቦች(ቡንደስሊጋ) መካከል ውድድር የለም።

ጨዋታ ባይኖርም፤ በመጪው የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ወደ ባየርን ሙዑንሸን የሚዛወረው የቦሩሲያ ዶርትሙንድ ታዋቁቂ የፊት አጥቂ ሮበርት ሌቫንዶብስኪ፣ ከተጠቀሰው ወቅት አንስቶ እ ጎ አ እስከ 2019 ለአዲሱ ክለብ ለመጫወት ባለፈው ቅዳሜ ተፈራርሟል።

Bildergalerie Fußballer Eusebio da Silva Ferreira
ምስል picture-alliance/AP Photo

በዓመት የሚያገኘው ደመወዝም 8 ሚሊዮን ዩውሮ መሆኑ ታውቋል። አምና ማሪዮ ገኧትዘ የተባለውን የዶርቱሙንድ የፊት አጥቂ ተጫዋች ዘንድሮም ሌቫንዶብስኪን ፣ ባየርን መግዛቱ በቡንድሊጋ በሌሎች ክለቦች እንዳይበለጥ ከማስላት አለመቆጠቡን ያሳያል የሚል ትችት በየጊዜው ሲቀርብ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ክርክር ሳይሆን ኳስ ጨዋታ ውድድር ነው ሲካሄድ የሰነበተው። የዛሬው ስፖርት አዘጋጅ ሃይማኖት ጥሩነህ ፣ ስለእግር ኳስና ሌሎችም ሳምንታዊ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ያሰናዳችውን ዝግጅት ታቀርብልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ