1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2006

ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ ፀጋዮ ከበደ በሶስተኛነት አየለ በሽር ደግሞ በአራተኛነት ጨርሰዋል ። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባም ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቃለች ። አትሌት ኃይለ ሥላሴ ደግሞ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል ።

https://p.dw.com/p/1BhvI
Fußball Bundesliga 30. Spieltag: Bayer 04 Leverkusen - Hertha BSC
ምስል P.Stollarz/AFP/Getty Images

ትናንት በተካሄደው 34 ተኛው የለንደን ማራቶን ኬንያውያን ድርብ ድል ተቀዳጅተዋል በወንዶች ማራቶን ውድድሩን በወንዶች ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ በሴቶች ደግሞ ኢድና ኪፕላጋት በአንደኛነት ጨርሰዋል ዊልሰን ኪፕሳንግ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ክብረ ወሰንም ነው የሰበረው ለሁለተኛ ጊዜ የለንደን ማራቶን ባለድል ኪፕሳንግ ውድድሩን የጨረሰው 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 24 ሴኮንድ ነው ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን አሸናፊ ፀጋዮ ከበደ በሶስተኛነት አየለ በሽር ደግሞ በአራተኛነት ጨርሰዋል አትሌት ጥሩነሽ ዲባባም ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቃለች አትሌት ኃይለ ሥላሴ ደግሞ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል ኬንያውያን ድል የተቀዳጁበት 34ኛው የለንደን ማራቶን እንዲሁም፣ የእንግሊዝ የጀርመን እና የስጳኝ የእግር ኳስ ክበቦች ጨዋታ የሳምንታዊው የስፖርት ዜግጅታችን ትኩረት ነው

ሃና ደምሴ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ