በአማራ ክልል ሴቶችን በሥልጣን የማሳተፍ ጥያቄ
ሰኞ፣ የካቲት 22 2013ማስታወቂያ
ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ እኩል ተሳታፊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት መልካም ጅምር ቢሆንም፣ በዝቅተኛው የመንግሥት መዋቅር አሁንም ጉድለቶች እንዳሉ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አስታወቀ፣ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ በፖሊሲና በስልት የተነደፉ አሰራሮች ወደ ተግባር እንዲለወጡ ትግል አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡ በባሕር ዳር ከተማ ዛሬ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኤፌድሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገሥ የሴቶችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ በፖሊሲና በስልት ቢደገፍም ወደ ተግባር ለመቀየር ግን አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ በመጪው 6ኛው አገራዊ ምርጫም የአገሪቱ ሴቶች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ