በኢትዮጵያ አዲሱ የሰላም ሂደት ኤርትራውያን ስደተኞች ሆነው የመቀጠላቸው ጥያቄ
ድንገተኛው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም እንዲሁም ተዘግተው የቆዩት አደገኛ ድንበሮች መከፈት [በአሁኑ ወቅት የተዘጉ ቢኾንም] የተስፋ እና የአዎንታዊ መንፈስ ማዕበልን በሁለቱም ሃገራት አሰራጭቷል። ሆኖም ግን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ኤርትራውያን አሁንም ጥገኞች ናቸው የሚል አዲስ ጉዳይ ብቅ ብሏል።
አስመራ! አስመራ! አስመራ!
ከኤርትራ ጋር ድንበር በምትጋራው የኢትዮጵያ ክፍል ትግራይ ከተሞች ተሳፋሪ የሚጠሩ የመለስተኛ አውቶቡስ ረዳቶች አዲስ ጩኸት ጀምረዋል። እዚህ ማደሪያው ላይ ቤንዚኑን የሚሞላው መለስተኛ አውቶቡስ ከመቀሌ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደምትገኘው የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚጓዝ ነው። በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙት የታየው ታሪካዊ ለውጥ ማለት ኤርትራውያን በአንድ ወቅት እጅግ አደገኛ የነበረውን የድንበር አካባቢ ያለ ይለፍ ሰነድ ወይም ፈቃድ መሻገር ይችላሉ ማለት ነው።
በመጨረሻም የመንቀሳቀስ ነፃነት
ኤርትራውያን ወደ አሥመራ ከመጓዛቸው አስቀድመው የድንበር የፍተሻ ኬላ ላይ ተሰልፈዋል፤ ይህም ሁሉም ኤርትራውያን ኢትዮጵያ ውስጥ በጥገኝነት መኖር እንደማይፈልጉ ያመለክታል። «አጎቴ ከቤተዘመዶቻችን ጋር አብሮ እንዲኖር ወደ አሥመራ እየወሰድኩት ነው፤ እኔ ግን ወደ ኢትዮጵያ እመለሳለሁ።» ትላለች ኢትዮጵያዊ ካገባች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ የመጣችሁ ሰናይት። ሆኖም ግን ከጎርጎሪዮሳዊው 1998 እስከ 2000 ጦርነት ተካሂዶ ድንበሩ ከተዘጋ በኋላ ኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቿን ጎብኝታ አታውቅም።
ጉብኝት
የዘንባባ ዛፎች በሰልፍ የተሰደሩበት የመቀሌ ጎዳና ኤርትራውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ከመጓዛቸው አስቀድመው ነፍስ ያለበትን ማኅበራዊ ሕይወት የሚያጣጥሙበት መሰባሰቢያ ስፍራ ነው። ይህን ሁኔታ የተመቻቸ የሚያደርገው ደግሞ በጎርጎሪዮሳዊው 1993 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከመገንጠሏ በፊት በርካታ ኤርትራውያን እና የትግራይ ወገኖች የሚጋሯቸው እንደ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ባህል እና ማኅበራዊ ልማዶች በመኖራቸው ነው።
የጋራ መገለጫዎች እና ዘዬዎች
በተመሳሳዩ የፀጉር አሠራር እና አለባበስ ምክንያት በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ የሚታዩ የትግራይ እና ከኤርትራ ሴቶች ለመለየት አዳጋች ነው። «ከኤርትራውያን ጋር ጠንካራ መተሳሰር አለን» ይላል አብዛኞቹ የትግራይ ሰዎች ኤርትራውያን ዘመዶች እንዳሏቸው ኤርትራውያንም እንዲሁ እንዳላቸው የገለፀው የ35 ዓመቱ የመቀሌው ሁዬ በርሔ። «አንድ ሕዝብ ነን። በመነጠላቸው ያሳለፉት ስቃይ ይሰማኛል። በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦታቸው የተነጣጠሉባቸው ብዙ ጓደኞች አሉኝ።»
የጋራ መገለጫዎች እና ዘዬዎች
በተመሳሳዩ የፀጉር አሠራር እና አለባበስ ምክንያት በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ የሚታዩ የትግራይ እና ከኤርትራ ሴቶች ለመለየት አዳጋች ነው። «ከኤርትራውያን ጋር ጠንካራ መተሳሰር አለን» ይላል አብዛኞቹ የትግራይ ሰዎች ኤርትራውያን ዘመዶች እንዳሏቸው ኤርትራውያንም እንዲሁ እንዳላቸው የገለፀው የ35 ዓመቱ የመቀሌው ሁዬ በርሔ። «አንድ ሕዝብ ነን። በመነጠላቸው ያሳለፉት ስቃይ ይሰማኛል። በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦታቸው የተነጣጠሉባቸው ብዙ ጓደኞች አሉኝ።»
የጋራ መገለጫዎች እና ዘዬዎች
በተመሳሳዩ የፀጉር አሠራር እና አለባበስ ምክንያት በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ የሚታዩ የትግራይ እና ከኤርትራ ሴቶች ለመለየት አዳጋች ነው። «ከኤርትራውያን ጋር ጠንካራ መተሳሰር አለን» ይላል አብዛኞቹ የትግራይ ሰዎች ኤርትራውያን ዘመዶች እንዳሏቸው ኤርትራውያንም እንዲሁ እንዳላቸው የገለፀው የ35 ዓመቱ የመቀሌው ሁዬ በርሔ። «አንድ ሕዝብ ነን። በመነጠላቸው ያሳለፉት ስቃይ ይሰማኛል። በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦታቸው የተነጣጠሉባቸው ብዙ ጓደኞች አሉኝ።»
ሰላም እና ብልፅግና
«ንግዱ በጣም ግሩም ነው፣» ይላል ከመቀሌ ወጣ ብሎ በሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካ የሚሠራው ተስፋዬ። ሆኖም ግን በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የኢትዮጵያን ብር እና የኤርትራን ናቅፋ ድንበር አቅርጠው ለሚጓዙ መንገደኞች በመመንዘር ተጨማሪ ገንዘብ ያገኛል። «ባንኮች ገና የምንዛሪ አገልግሎት ስላልጀመሩ መልካም አጋጣሚ ነው።» የተከፈተው ድንበር በሁለቱም አቅጣጫ የንግድ እና ሸቀጥ ፍሰትን አይቷል።
መቀሌ ላይ በመኪና መሽከርከር
ER 1 የሚል የኤርትራ ሰሌዳ ያላቸው ያረጁ የሚመስሉ መኪናዎች ከመለስተኛ አውቶቡሶቹ ጎን ለጎን በትግራይ ዋና ጎዳናዎች ወደ ድንበሩ ሲጓዙ ወይም መቀሌ አካባቢ ይታያሉ። «እዚህ የኖሩ በርካታ ኤርትራውያን ነበሩ።» ይላሉ ማዕከላዊ መቀሌ ላይ ላሊበላ የተሰኘውን ሆቴልን በባለቤትነት የያዙት ሩታ። ሥራ ፈላጊ ኤርትራውያን በመበርከታቸው መቀሌ ላይ አሁን ክፍሎችን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ይታያል።
የተሰዳጆችን ጉዳይ ማካሄዱ ቀጥሏል
ትግራይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር በእንግሊዝኛው ምህጻር ARRA ባልደረባ የስደተኞችን የማመልከቻ ቅፅ ፎቶ ኮፒ ታደርጋለች። «ኢትዮጵያ የጄኔቫው የስደተኞች ውል ፈራሚ ናት፤ ስለዚህ ለጊዜው በስደተኝነት ይዞታቸው ላይ ለውጥ የለም» ይላሉ የARRA ባልደራ ተክኤ ገብረኢየሱስ። «የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ተሻሽሏል፤ ሆኖም ግን የኤርትራ የውስጥ ሁኔታ አሁንም ያው ነው።»
ትኩረት በማሻሻያው አራማጅ ጠቅላይ ሚኒስቴር ላይ
በምሣ ሰዓት ተመጋቢዎች ከኤርትራ ጋር ሰላም በማውረድ ሁሉን ያስደነገጡትን ታዋቂ የኢትዮጵያ መሪ የዐቢይ አህመድን ይመለከታሉ። ኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞችን በተመለከተ የገጠማት ፈተና የዓለም አቀፉን እውነታ ያንጸባርቃል። «ስደተኞች ሁልጊዜ ሰለባዎች ተደርገው ነው የሚገለፁት።» ትላለች የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ የምትመረምረው ሚሌይና ቤሎኒ። «እውነታው ችሎታ ይዘው፣ ሕልም፣ ምኞት እና ፍላጎቶቻቸውን ሰንቀው የመጡ ይመስላል።»
ስደተኞች እና ሰላም ተቃራኒ አይደሉም
ሴት ተማሪዎች በትግራይ ክልል የተመድ የስደተኞች ድርጅት UNHCR ጽሕፈት ቤት አጠገብ እየሄዱ ነው። ሃሳባቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የUNHCR ባልደረባ በመላው ዓለም የሚገኙ ሃገራት በጠቅላላ ማለት ይችላል ስደተኞች ከመጡበት ሀገር ጋር ሰላም ካላቸው ይህን ያደርጋሉ። እዚህም የሆነውም ያልተለመደ ነገር አይደለም፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም አውርደውም የስደተኞች ፍሰቱ ቀጥሏል።
ሁለቱንም ሃገራት ማጠናከር
ከመቀሌ ከተማ ውጭ የሚከናወነው ግንባታ። የኤርትራውያን የስደተኝነት ይዞታ ምን ይሁን ምን ድንበሩ በመከፈቱ የመቀሌ እና የአሥመራ የወደፊት የኤኮኖሚ ሁኔታ መጠናከር አለበት። ምናልባት ወደፊት የበለጡ ተግዳሮቶች ሊኖሩ ይችላሉ። «የኤርትራ መንግሥት ወደኋላ የሚመለስበት መንገድ ያለው አይመስለኝም» ትላለች መቀሌ ላይ የምትገኘው የንግድ ባለቤት ትበርህ። «ኤርትራውያን ነፃነትን እያጣጣሙ ነው፤ ለውጡ አይቀለበስም።»
ሁለቱንም ሃገራት ማጠናከር
ከመቀሌ ከተማ ውጭ የሚከናወነው ግንባታ። የኤርትራውያን የስደተኝነት ይዞታ ምን ይሁን ምን ድንበሩ በመከፈቱ የመቀሌ እና የአሥመራ የወደፊት የኤኮኖሚ ሁኔታ መጠናከር አለበት። ምናልባት ወደፊት የበለጡ ተግዳሮቶች ሊኖሩ ይችላሉ። «የኤርትራ መንግሥት ወደኋላ የሚመለስበት መንገድ ያለው አይመስለኝም» ትላለች መቀሌ ላይ የምትገኘው የንግድ ባለቤት ትበርህ። «ኤርትራውያን ነፃነትን እያጣጣሙ ነው፤ ለውጡ አይቀለበስም።» ጄምስ ጄፈሪ/ሸዋዬ ለገሠ
ድንገተኛው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም እንዲሁም ተዘግተው የቆዩት አደገኛ ድንበሮች መከፈት [በአሁኑ ወቅት የተዘጉ ቢኾንም] የተስፋ እና የአዎንታዊ መንፈስ ማዕበልን በሁለቱም ሃገራት አሰራጭቷል። ሆኖም ግን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ኤርትራውያን አሁንም ጥገኞች ናቸውን የሚል አዲስ ጉዳይ ብቅ ብሏል።