በኤርትራ ማዕቀብ መነሳት እነማን ሚና ነበራቸው ?
ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2011የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታዉ ምክርቤት የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በኤርትራ ላይ ማዕቀቡን ያሳረፈዉ፤ ኤርትራ በጎረቤት ሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉን የደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብን ትረዳለች በሚል እና ኤርትራ ከጅቡቲ ጋራ ያላትን የድንበር ዉጥግብ ለመፍታት ጥረት አላደረገችም በሚል ነበር ። ማዕቀቡ የጦር መሳርያና ግዥ ማዕቀብንና፤ ባለሥልጣናት ወደ ዉጭ ሃገር እንዳይጓዙ የሚከለክል እንዲሁም በዉጭ ሃገራት የሚገኝ ሃብታቸዉ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ነዉ።
የማዕቀቡን መነሳት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ ህዝብና መንግስት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አማካኝነት የተላለፈው መግለጫ የማዕቀቡ መነሳት በአፍሪቃ ቀንድ ለሚታየው መረጋጋት እና ሰላም ዘለቄታዊነት ብሎም በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብሏል።
ከውሳኔው መተላለፍ አስቀድሞ የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ አንድ የኢትዮጵያ የቀድሞ ዲፕሎማት እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሞያን አነጋግሮ ነበር። ማዕቀቡ እንደሚነሳ ቅድሚያ ግምታቸውን ሰጥተው የነበሩት ሁለቱ የፖለቲካ ታዛቢዎች ለዚህም ምክንያቶች ናቸው ያሏቸውን አብራርተዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
መክብብ ሸዋ
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ