ባለስልጣን የተገደለበት የታጣቂዎች ጥቃት በምዕራብ ወለጋ ዞን
ማክሰኞ፣ ግንቦት 10 2013ቅዳሜ ግንቦት 7/2013 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ቆንዳላ ወረዳ የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ኃላፊን አቶ ዋቅጋሪ ቀጀላን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸንም የዞኑ አስተዳደር አመለከተ፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ ጥቃጡ የተፈጸመው አመራሮቹ ለስራ ወደ መንዲ እና ቆንዳላ መስመር ባቀኑበት ወቅት ነበር፡፡ በዕለቱ የምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ አካባቢ በማዕድን ማውጣት ሰራ የተሰማሩ ሶስት ቻይኖች ታግተዋል ተብሎ በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ ሲገለጽ የቆየው መረጃ በተመለከ በዞኑ ውስጥ የታገተ ሰው አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ የተያዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን በዞናችን ውስጥ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ታገቱ የተባሉ የቻይና ዜጎች በአሶሳ ዞን ኦዳ ብልድግሉ በተባለ ወረዳ መሁኑን በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ዜደዎችም ሲገለጽ ቆይተዋል፡፡ ይህንን መረጃ ለማጣራት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና ወደ ክልሉ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ስልክ በተደጋጋሚ ደውየ ነበር ስልክ ባለመመለሳቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት ሰባት/2013 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ቆንዳላ እና መንድ ከተማ መስመር ለስራ በተንቀሳቀሱ የዞኑ ስራ ሀላፊዎች እና ሚሊሻዎች ላይ በተፈጠመው ጥቃት በሰው ጉዳት መድረሱን አቶ ኤሊያስ ገልጸዋል፡፡ የምዕራብ ወለጋ መንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣን ኃላፈ እና 2 ሚሊሻዎች ሌላ አንድ ሰው ሸማቂዎች ባደረሱት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ዙሪያ በተመሳሳይ ቀን ወርቅ በማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ነበር የተባሉ የቻይና ዜጎች ታገቱ ተብለው የሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሌያስ ኡመታ በስልክ ለዲዳቢው ተናግረዋል፡፡ በተጠቀሰው ስፋራ በወቅር ማውጣት የተሰማራ የውጭ ዜጋ አለመኖራን ያብራሩት ኃላፊው የጸጥታ ሀይሎችና ባለሙያዎች ባደረጉት ማጣራት ተፈጸመ የተባለው እገታ በዞናቸው ውስጥ እንዳልሆነ አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ በማእድን ማውጣት ስራ የተሰማሩ ሰዎች ታግተዋል መባሉን ከማበህራዊ መገናኛ ዘዴ መስማታቸውንና ከዞኑ ውጭ አጎራባች በሆኑ ወረዳዎች በኢንቨስትመንት ስራ የተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችለም ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው በሰጡን ማብራሪያ በዜጎች ላይ ጥቃት በሚያርሱ ጸረ ሰላም ባሏቸው አካላት ላይ በተቀናጀ መልኩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡ ሰሙኑን በምእራብ ወለጋ ጥቃት መፈጸሙን ያረጋገጡት ኃላፊው ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ሀይሎች ለህግ የማቅረብ እና ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የማድረግ ስራ እየተሰራ እደሆነም አክለዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ በመጋቢት ወር በአንድ ወረዳ ውስጥ በደረሰው ጥቃት በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱም የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫው ጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ መውደሱን ገልጾ ነበር፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ