1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተመረዙ የተባሉት የፑቲን ዋና ተቃዋሚ ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 2012

ጀርመን ዉስጥ በሕክምና ላይ የሚገኙት የሩሲያ መንግስት ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልንይ በሩሲያ  ባለስልጣናት ሳይመረዙ አይቀርም የሚለዉን ጥርጣሬና ወቀሳ ባለስልጣናቱ ዉድቅ አረደጉት።የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ተቃናቃኝ የተባሉት ናቫልንይ ባለፈዉ ሐሙስ አዉሮፕላን ዉስጥ እራሳቸዉን ስተዉ ከወደቁ ወዲሕ እስካሁን እራሳቸዉን አያዉቁም።

https://p.dw.com/p/3hV1P
Russland Alexej Nawalny
ምስል Reuters/S. Zhumatov

በርሊን-ጀርመን ዉስጥ በሕክምና ላይ የሚገኙት የሩሲያ መንግስት ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልንይ በሩሲያ  ባለስልጣናት ሳይመረዙ አይቀርም የሚለዉን ጥርጣሬና ወቀሳ ባለስልጣናቱ ዉድቅ አረደጉት።የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ተቃናቃኝ የተባሉት ናቫልንይ ባለፈዉ ሐሙስ አዉሮፕላን ዉስጥ እራሳቸዉን ስተዉ ከወደቁ ወዲሕ እስካሁን እራሳቸዉን አያዉቁም።ሕመምተኛዉ ከኦማስክ-ሩሲያ ፣ በርሊን-ጀርመን ሻሪቴ ሆስፒታል ከመጡ ወዲሕ የመረመሯቸዉ የጀርመን ሐኪሞች ሰዉነታቸዉ ዉስጥ መርዛማ ንጥረ ነገር ማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል።ወትሮም የሩሲያ መንግስትን የሚጠጥሩት የናቫልንይ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች የሐኪሞቹን ጥቆማ ለጥርጣሬያቸዉ ማረጋገጪያ አድርገዉ የሩሲያ መንግስትን እየወቀሱ ነዉ።የጀርመንዋ መራሒተ መንግስት አንጌላ ሜርክልና የሌሎች የምዕራባዉያን መንግሥታት መሪዎች በበኩላቸዉ ሩሲያ ጉዳዩን እንድታጣራ ጠይቀዋል።የክሬምሊን ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ ግን ወቀሳ፣ትችቱን «ባዶ ጫጫታ» በማለት ዉድቅ አድርገዉታል።ምርመራ ይደረግ ለሚለዉ ጥሪ የሰጡት መልስ ደግሞ «ለምርመራ ምክንያት ያስፈልጋል» የሚል ነዉ። 

Deutschland Nawalny | Charite in Berlin
ምስል Reuters/M. Tantussi

 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ