1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ክፍለ ማርያም፤ ኢትዮጵያዊዉ ምሁር በጀርመን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 29 2013

በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ በሁለት የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጋዜጠኝነት ይሰሩ ነበር።አቶ ክፍለማርያም መጀመሪያ ላይ በሰለጠኑበት የእርሻ ሞያ ሀገራቸው ገብተው መስራቱ ባይሳካላቸውም የጋዜጠኝነቱን ሥራ ትተው እዚያው ጀርመን በተሰማሩበት የልማት ሥራ አማካይነት በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ካገለገሉ በኋላ ኢትዮጵያ የመሥራት እድልም ገጥሟቸዋል።

https://p.dw.com/p/3w7SZ
Äthiopien Kiflemariam Gebrewold
ምስል Privat

አቶ ክፍለ ማርያም ገብረ ወልድ ፦ ጋዜጠኛ፣የልማት አጥኚ የፖለቲካ ሳይንስና የግብርና ምሁር

አቶ ክፍለ ማርያም ገብረ ወልድ ጀርመን ከመጡ ግምሽ ምዕተ ዓመት አልፏል። አዲስ አበባ ከሚገኘው ጀርመን ትምሕርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን  የጨረሱት አቶ ክፍለ ማርያምና ሌሎች ጓደኞቻቸው ከፍተኛ ትምሕርት ለመከታተል በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በመጡባት ጀርመን ጥቂት ዓመታት ተመርው ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በቀሰሙት እውቀት ሃገራቸው መስራት ነበር እቅዳቸው።
አቶ ክፍለ ማርያምና ጓደኞቻቸው እንደ ፍላጎታቸው ተማሩ።ወደ ሃገራቸው የመመለስ እቅዳቸው ግን ሳይሰምር ቀረ። ይህ ሰበብ ሆኖ ጀርመን ሲቀሩ ጌዜአቸውን ላለማባከን ከፍተኛ ትምሕርታቸውን ወዲያውኑ ቀጠሉ። ትምህርት ላይ ሳሉ አንስቶ በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ በሁለት የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጋዜጠኝነት ይሰሩ ነበር።አቶ ክፍለማርያም መጀመሪያ ላይ በሰለጠኑበት የእርሻ ሞያ ሀገራቸው ገብተው መሥራቱ ባይሳካላቸውም የጋዜጠኝነቱን ሥራ ትተው እዚያው ጀርመን በተሰማሩበት የልማት ሥራ  በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ካገለገሉ በኋላ ኢትዮጵያ የመስራት እድልም ገጥሟቸዋል።አቶ ክፍለማርያም ገብረ ወልድ አዲስ አበባ ነው የተወለዱት።ያደጉት ፓፓላሬ በሚባለው ሰፈር ነው።የአንደኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን በካቴድራልና በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤቶች ነው የተከታተሉት።ሁlt,ኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባው የጀርመን ትምሕርት ቤት ነው ያጠናቀቁት ጀርመን ለከፍተና ትምህርት ከመምጣታቸው አስቀድሞ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋና ጸሀፊ የነበሩት ወንድማቸው አቶ ከበደ ገብረወልድ ጋ በመጡበት አጋጣሚ ለአንድ ዓመት ቦን የመማር እድል አግኝተው ነበር።ለመሆኑ እርሳቸው ጀርመን በመጡበት ዘመን የዛሬ 50 ዓመት የነበረችው ጀርመንና የአሁኒቷ ጀርመን  በምን ይለያዩ ይሆን?አቶ ውብነህ ገረሱ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት ከአቶ ክፍሉ ጋር ለትምህርት ጀርመን ከመጡት ጓደኞቻቸው አንዱ ናቸው።የእርሻ ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ በዚያው የትምሕርት መስክ ቀጥለው በግብርና ምህንድስና ተመርቀዋው እዚሁ ጀርመን በተለያዩ  ድርጅቶች ሰርተዋል።ከልጅነት አንስቶ የሚያውቋቸውን  አቶ ክፍለ ማርያምን እንዲህ ገልጸዋቸዋል።አቶ ታምሩ በሻህ አቶ ክፍሉን በ1970ዎቹ ነውከአቶ ክፍለ ማርያም ጋር የተዋወቁት። ያኔ ሁለቱም ተማሪዎች ነበሩ።ጀርመን ሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ያጠኑት አቶ በሻህ ኢትዮጵያ በሶላር ፕሮጀክቶች ላይ በሰሩበት በጎርጎሮሳዊው ከ2010 ዓመት ምህረት በኋላ አቶ ክፍለማርያምም የልማት አማካሪ ሆነው  በሰሩበት አጋጣሚ ይበልጥ ተቀራርበው እንደነበር ይናገራሉ።አቶ ክፍለ ማርያምን እርሳቸውም ዝምተኛ ሲሉ ነው የገለጿቸው።በአሁኑ ጊዜ በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ክፍለማርያም ገብረ ወልድ ከዚህ በፊት በሚሰሩባቸውና በሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በልማት ስራዎች አማካሪነት በግል እየሰሩ ነው። ከዚህ ሌላ በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተሟቋት ያስተምራሉ ተማሪዎችንም ያማክራሉ። ባለትዳርና የሁለት ሴቶች ልጆች አባትም ናቸው።
ኂሩት መለሰ

Äthiopien Kiflemariam Gebrewold
ምስል Privat
Äthiopien Kiflemariam Gebrewold
ምስል Privat

እሸቴ በቀለ