አፍሪቃዊቷ ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋገጠች
ማክሰኞ፣ ኅዳር 20 2015ማስታወቂያ
አፍሪቃዊቷ ሴኔጋል እና ኔዘርላንድስ ከምድብ «ሀ» አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋገጡ። ዛሬ በተደረጉት ሁለት ግጥሚያዎች ሴኔጋል ኤኳዶርን 2 ለ1 ድል ስታደርግ፤ ኔዘርላንድስ ቀጠርን 2 ለ0 ማሸነፍ ችላለች። በዚህ ምድብ ኔዘርላንድ 7 ነጥብ እና 4 የግብ ክፍያ ሲኖራት፤ ሴኔጋል 6 ነጥብ እና 1 የግብ ክፍያ ማግኘት ችላለች። በዚህም መሠረት ኔዘርላንድ ከምድቡ 1ኛ ሴኔጋል 2ኛ ሆነው አልፈዋል።
ለሴኔጋል ቀዳሚዋን ግብ በ44ኛው ደቂቃ ላይ ኢሳሚይላ ሣር እንዲሁም የማሸነፊያዋን ግብ በ70ኛው ደቂቃ ላይ ካሊዱ ኩሊባሊ አስቆጥረዋል። ሞይሰስ ካይሴዶ ለኤኳዶር ብቸኛዋን ግብ 67ኛው ደቂቃ ላይ ቢያስቆጥርም ኤኳዶር በ4 ነጥብ የምድቡ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ 0 ነጥብ ካላት አስተናጋጇ ቀጠር ጋር ተሰናብቷል። ኢራን ከአሜሪካ እንዲሁም ዌልስ ከእንግሊዝ ጋር ከሰዓታት በኋላ የሚያደርጓቸው ሁለት ጨዋታዎች በበርካቶች ዘንድ ይጠበቃሉ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ