1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የአልጀርስን ስምምነት ስለመቀበሏ የአውሮጳ ህብረት አስተያየት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2010

የአውሮጳ ህብረት ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በድንበር ሰበብ የተካሄደውን ጦርነት ያስቆመውን የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በ1993 ዓም በአልጀሪያ መዲና አልጀርስ የተፈራረሙትን ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሏን አሞገሰ።

https://p.dw.com/p/2zr2W
12.10.2012 DW Symbolbild Flagge EU Europäische Union Himmel

«ለሰላሙ ሂደት መሳካት የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ የበኩላቸውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።»

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ግንባር፣ ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት የተሰየመዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን የሰጠውን ብይን የኢትዮጵያ መንግሥት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ ያደረገበትን ውሳኔ የአውሮPA ህብረት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም ለማውረድ የተወሰደ ትልቅ ርምጃ አድርጎ ተመልክቶታል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ክሌ

አዜብ ታደሰ