1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወሰዷቸው የተባሉት የጦር እርምጃዎች፣

ሐሙስ፣ ግንቦት 30 2004

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል፣ ለ 11 ዓመታት የዘለቀው »ሰላም የለም ጦርነት የለም ሁኔታ » ታደሰ እንግዳው እንደዘገበልን በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት እየተበላሸና ወደ ውጥረት እየተሸጋገረ ነው ሲሉ አንዳንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የፖለቲካ

https://p.dw.com/p/15AJu
ምስል AP Graphics/DW

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል፣ ለ 11 ዓመታት የዘለቀው »ሰላም የለም ጦርነት የለም ሁኔታ » ታደሰ እንግዳው እንደዘገበልን በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት እየተበላሸና ወደ ውጥረት እየተሸጋገረ ነው ሲሉ አንዳንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ። ሁለቱ ወገኖች አንዱ የሌላውን ድንበር በመሻገር ጥቃት ስለመፈፀሙ በሰው ና ንብረትም ላይ ጉዳት ስለ መድረሱ ይነገራል ። ይሁንና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁት እንደሌለ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ተፈፀመ ስለተባለው ጥቃት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።

ታደሰ እንግዳው
ተክሌ የኋላ
ሸዋዮ ለገሰ