1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና ኤርትራ ጥሩ ግንኙነት ላይ ናቸዉ ተባለ 

ዓርብ፣ ሐምሌ 19 2011

ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለዉ የሕዝብ ለሕዝብም ሆነ የመንግሥታቱ ግንኙነት በአመርቂ ደረጃ ላይ መሆኑን በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲየታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ገለፁ። ወ/ሮ ሂሩት ይህን የተናገሩት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመሥርያ ቤታቸዉን የአንድ ዓመት የሥራ ክንዋኔ በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3Mnb7
Äthiopien und Eritrea Frieden Logo
ምስል DW/S. Fekade

ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ የሚሄዱ ኢትዮጵያን መብትን ጉዳይ ሌላዉ ርዕስ ነበር

ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለዉ የሕዝብ ለሕዝብም ሆነ የመንግሥታቱ ግንኙነት በአመርቂ ደረጃ ላይ መሆኑን በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲየታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ገለፁ። ወ/ሮ ሂሩት ይህን የተናገሩት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመሥርያ ቤታቸዉን የአንድ ዓመት የሥራ ክንዋኔ በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ነዉ። ሃያ ዓመታት ግንኙነት ያልነበራቸዉ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ይፈፀማል ያሉት ነገር በቀነ ቀጠሮ መሰረት ላይፈፀም ይችላል ሲሉም ሚኒስትር ዲየታዋ አስረድተዋል። በመግለጫዉ ላይ ከተነሱት በርካታ ነጥቦች መካከል የሥራ ፈቃድ አግኝተዉ ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ የሚሄዱ ኢትዮጵያን መብትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ስላዉ ጉዳይም አብራርተዋል። መግለጫዉን የተከታተለዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ 
ተስፋለም ወልደየስ