1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ለአሸባብ መሣሪያ በማቀበል መወንጀሏ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 23 2004

የኬንያ መገናኛ ብዙሀን ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት የጦር መሣሪያ የጫኑ አውሮፕላኖች በተከታታይ ሶማሊያ ማረፋቸውን በመዘገብ ላይ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/Rujx
ምስል AP Graphics/DW

በነዚሁ ዘገባዎች መሠረት የጦር መሳሪያዎቹ የተላኩት ለአሸባብ ሲሆን ምንጫቸውም ኤርትራ መሆኗ ተደጋግሞ ተወስቷል ። የዶቼቬለ የኪስዋህሊ ክፍል የናይሮቢ ዘጋቢ እንዳለው የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘገባዎቹን ያቀረቡት የኬንያ ጦር በዜና ምንጭነት በመጥቀስ ነው ። ኤርትራ በበኩሏ ዘገባዎቹን ሃሰት ስትል አስተባብላለች ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ