1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር የሆነችበት 29ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ሰኞ፣ ግንቦት 17 2012

ኤርትራ ሉዓላዊ ሀገር የሆነችበት 29ኛ ዓመት ክብረ በዓል ትላንት በይፋዊ ስነ ስርዓት በአስመራ ተከበረ፡፡"እየመከትን እንጓዛለን" በሚል መሪ ሐሳብ የተከበረው ይኽ 29ኛ ዓመት 'የነፃነት ቀን' በኮረና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ካለፉት ዓመታት በተለየ በአስመራ ሲነማ ሮማ የተለያዩ መልእክቶች በማስተላለፍና በኪነት ስራዎች ተዘክሯል፡፡

https://p.dw.com/p/3cjwl
Eritrea Bevölkerung feiert Referendum 1993
ምስል Getty Images/AFP/A. Joe

29ኛው ዓመት የኤርትራ ነጻነት ቀን ሲከበር

ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር የሆነችበት 29ኛ ዓመት ክብረ በዓል ትላንት በይፋዊ ስነ ስርዓት በአስመራ ተከበረ፡፡"እየመከትን እንጓዛለን" በሚል መሪ ሐሳብ የተከበረው ይኽ 29ኛ ዓመት 'የነፃነት ቀን' በኮረና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ካለፉት ዓመታት በተለየ በአስመራ ሲነማ ሮማ የተለያዩ መልእክቶች በማስተላለፍና በኪነት ስራዎች ተዘክሯል፡፡በዚሁ በዓል የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ባስተላለፉት መልእክት ኤርትራ አካባቢያዊና ዓለምአቀፋዊ ለውጥ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮረና  ወረርሽኝ  አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታው ለመገንዘብ አስቸጋሪ በመሆኑ ሀገራቸው በሽታውን በመከላከል ላይ ትኩረት አድርጋ በመስራቷ ውጤት ማስመዝገቧን ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች በአሁኑ ወቅት ኤርትራ በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ይገልፃሉ፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ