ኤርትራ በአሜሪካ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ተባባሪ አይደሉም ከተባሉ አገራት ዝርዝር ወጣች
ቅዳሜ፣ ግንቦት 24 2011ማስታወቂያ
ኤርትራ በአሜሪካ አሸባሪነትን ለመዋጋት ተባባሪ አይደሉም ተብለው ከተፈረጁ አገሮች ዝርዝር ወጥታለች። በዚህ የአሜሪካ ዝርዝር ውስጥ ሶርያ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ይገኙበታል። አሜሪካ ኤርትራን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ተባባሪ አይደሉም ከምትላቸው አገራት ጎራ ያስቀመጠችው ከሁለት አመታት ገደማ በፊት ነበር። ለአሜሪካ ውሳኔ ዋንኛው ገፊ ምክንያት ኤርትራ የሶማሊያውን አል-ሸባብ ትደግፋለች በሚል የሚቀርብባት ውንጀላ ነው። የሶማሊያን መንግሥት ለመጣል የሚንቀሳቀሰው አል-ሸባብ በአሜሪካ አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ መካከል ይገኝበታል።
ሙሉውን ዘገባ ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ