1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከአምነስቲ ለኤርትራ የቀረበ ጥሪ 

ረቡዕ፣ መስከረም 7 2012

የኤርትራ መንግሥትን በመተቸታቸዉ እና በመቃወማቸዉ ምክንያት ለእስር የተዳረጉት 28 ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ይፈቱ ዘንድ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋዊ ዘመቻዉን ትናንት ጀመረ።

https://p.dw.com/p/3PnxG
Amnesty international
ምስል picture-alliance/dpa/W.Kumm

ከታሰሩ 18 ዓመት የሞላቸዉ ኤርትራዉያኑ መኖር መሞታቸዉ አይታወቅም

የኤርትራ መንግሥትን በመተቸታቸዉ እና በመቃወማቸዉ ምክንያት ለእስር የተዳረጉት 28 ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ይፈቱ ዘንድ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋዊ ዘመቻዉን ትናንት ጀመረ። ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የተጀመረዉ የዚህ ዘመቻ ዓላማ ታሳሪ ጋዜጠኛና ፖለቲከኞቹ በሕይወት ካሉ እንዲፈቱ፤ ከሞቱም መንግስት ትክክለኛዉን መረጃ ለቤተሰቦቻቸዉ ያደርስ ዘንድ ለመጠየቅ መሆኑን « አምነስቲ »  ዘመቻዉን በይፋ ሲያስጀምር አስታዉቆ ነበር። የዘመቻዉን እንደምታ በተመለከተ ታምራት ዲንሳ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ተጠሪን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናክሮአል።    


ታምራት ዲንሳ


አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ