1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2024 ዓ.ም ዐበይት ክስተቶች አንድምታቸውና መዘዞቻቸው

እሑድ፣ ታኅሣሥ 20 2017

2024 ዓ.ም. በዓለማችን ከባድ ጦርነቶች የቀጠሉበት ዓመት ነው።የፊታችን የካቲት ፣3 ዓመት የሚደፍነው የዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ከዓመት በላይ የዘለቀውና የአካባቢውን ሀገራት ያዳረሰው የእስራኤል ሀማስ ጦርነትና ዓመት ከ8 ወር ያለፈው የተዘነጋው የሱዳን ጦርነት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።የእነዚህ ጦርነቶች ዳፋም ለመላው ዓለም ተርፏል።

https://p.dw.com/p/4odbN
Ukraine-Krieg | Russland Grenzgebiet der Region Kursk
ምስል Russian Defense Ministry/AP/picture alliance

የ2024 ዓ.ም ዐበይት ክስተቶች አንድምታቸውና መዘዞቻቸው

ጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም ተሰናብቶ ስፍራውን ለቀጣዩ 2025 ዓም ሊያስረክብ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተዋል። ተነገ ወዲያ ማክሰኞ እኩለሊት የምንሰናበተው 2024 ዓለማችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አይታው የማታውቃቸው  ከባድ ጦርነቶች የቀጠሉበት በዚህ ሰበብም በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ሚሊዮኖች  ቀያቸውን ለቀው የተሰደዱበት ዓመት ነው። 

የፊታችን የካቲት ፣3 ዓመት የሚደፍነው የዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ ከዓመት በላይ የዘለቀውና ወደ ሊባኖስም የተስፋፋውና የመን ኢራንንና ሌሎች የአካባቢውን ሀገራት ያዳረሰው የእስራኤል ሀማስ ጦርነት እንዲሁም  ዓመት ከስምንት ወር ያለፈው የተዘነጋው የሱዳን ጦርነት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። የእነዚህ ጦርነቶች ዳፋም ለመላው ዓለም ተርፏል ማለት ይቻላል።

በየአካባቢያቸው በሚኖር ህዝብ ላይ ካደረሱት ሞት የአካል ጉዳትና ልዩ ልዩ ሰቆቃዎች ባሻገር ጦርነቶቹ በተቀረው ዓለም ላይም ያስከተሉት የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ክስተት ሆኗል።  

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል Aaron Chown/PA Wire/picture alliance

በእጥፍ የጨመረው የአውሮጳ ሀገራት የጦር መሣሪያ ግዥ

የሶሪያው መሪ በሽር አል አሳድ ከሀገራቸው መኮብለልና አማጽያኑ ብዙም ሳይዋጉ ሀገሪቱን መቆጣጠራቸው በዚህ ዓመት ዓለምን ካስደመመው ክስተቶች አንዱ ነው፤ የትራምፕ ወደ ሥልጣን መመለስም እንዲሁ።የጀርመን ጥምር መንግሥት ፈርሶ ያልተጠበቀ  ምርጫ መጠራቱ፣ የፈረንሳይ ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶችዋ መገፋት በዓመቱ ትኩረት የሳቡ ተጨማሪ ክስተቶች ናቸው ።ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣ የምዕራብ-ምሥራቆች ፍጥጫ አብነት

በጋዛ የመኖሪያ አካባቢ ላይ የተፈጸመ የእስራኤል ጥቃት
በጋዛ የመኖሪያ አካባቢ ላይ የተፈጸመ የእስራኤል ጥቃት ምስል Omar Ashtawy/apaimages/IMAGO

የዛሬው እንወያይ  የእነዚህንና የሌሎችንም የዓመቱን ዐበይት ክስተቶች አንድምታዎችና መዘዞቻቸውን ይዳስሳል። በ2025 ዓም ምን እንደሚጠበቅም ይመለከታል።  በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ የምጣኔ ኃብትና አስተዳደር ባለሙያ ከበርሊን፣አቶ አብዱራህማን ሰዒድ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር  የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ ከለንደን ፣ገበያው ንጉሴ  የዶቼቬለ የብራሰልስ ዘጋቢ እንዲሁም የዶቼቬለ የዋሽንግተን ዘጋቢ አበበ ፈለቀ ናቸው።

 

ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ 

ኂሩት መለሰ