1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሑመራ - ኦምሓጀር መንገድ መከፈት አንደምታ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል ወደ ኤርትራ የሚወስደው የሑመራ ኦምሓጀር መንገድ መከፈቱ ከሚኖረው ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ፋይዳ በተጨማሪ የተለየ ፖለቲካዊ መልእክት የሚያስተላልፍ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

https://p.dw.com/p/3BCvz
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed empfängt Eritreas Präsident Isayas Afewerki
ምስል Getty Images/AFP/E. Soteras

የሑመራ - ኦምሓጀር መንገድ መከፈት አንደምታ

በትላንትናው ዕለት በይፋ የተከፈተው ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚያገናኘው የሑመራ-ኦምሓጀር መንገድ ለአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል። በሌላ ጊዜ በአሁኑ ወቅት ድንበሩ መከፈቱ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለDW አስተያየታቸውን የሰጡ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

በሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ስራ የተሰማራው የሑመራ ከተማ ነዋሪው አቶ ዳንኤል ነጋሽ በሁለቱ ሀገራት መካከል ስምምነት ተደርጎ በዛላምበሳ እና ራማ በኩል የየብስ ግንኙነት ተጀምሮ ለምን በእኛ አካባቢ ድንበሩ አልተጀመረም የሚል ጥያቄ በሑመራ ህዝብ ይቀርብ እንደነበር ይገልጻል። ይሁንና ትላንት ሲጠበቅ የነበረው ድንበር ሲከፈት ህዝቡ ላይ ጥርጣሬ የፈጠረ፣ ያልተጠበቀ አጋጣሚ በመታየቱ ወጣቶች የተቃውሞ ድምጽ ማሰማታቸውን ይናገራል። በትላትናው የመንገድመክፈቻ ስነ ስርዓት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መታደም ተቃውሞ ማስነሳቱንም አክሏል። 

በትላንትናው የመክፈቻ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ተገኝተዋል።  የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መሥተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና የኢትዮጵያው ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ስነ ስርዓቱን ከታደሙ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ይገኙበታል።

የሑመራ ነዋሪዎችን እና የከተማይቱ ምክትል ከንቲባን ያነጋገረው የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ያጠናቀረውን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ተስፋለም ወልደየስ 

አርያም ተክሌ