የሰላም ማብሰሪያው ዝግጅት ታዳሚያን አስተያየት
ሰኞ፣ ሐምሌ 9 2010ማስታወቂያ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት ሲያደርጉት የቆዩትን ጉብኝት ዛሬ ረፋዱን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም መውረዱን ለማብሰር ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ዝግጅት የታደሙ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የሰላም ጥሪ ከልብ በመነጨ ስሜት ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ ለነበሩት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስም የድጋፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙም ነበር። የትላንትናውን ምሽት ሥነ-ስርዓት በቦታው በመገኘት የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የታዳሚያንን አስተያየት አሰባስቧል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተስፋለም ወልደየስ
አዜብ ታደሰ