1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰኞ ታኅሣሥ 23 ቀን፣ 2010 ዓ.ም. ስፖርት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2010

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ግስጋሴውን እንደቀጠለ ነው። እስካሁን በፕርምየር ሊጉ ካደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 19 በድል ተወጥቷል። የ2017 ዓመት ትናንት ሲጠናቀቅ 102 ጎል ከመረብ አሳርፏል። በአንፃሩ ቸልሲ የሊጉን ክብር ባለፈው የጨዋታ ዘመን ማግኘቱ አይዘነጋም። ነገር ግን የአንቶንዮ ኮንቲ ቡድን ማሽቆልቆሉን ተያይዟል። 

https://p.dw.com/p/2qBuQ
Premier League - Newcastle United vs Manchester City
ምስል Reuters/S. Heppell

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

ትላንት በተሸኘነው የጎርጎሮሳዊው 2017 አመት በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ የማይነካ አንበሳ ሆኖ ሽቅብ እየተንደረደረ ነው። እስካሁን በፕሪምየር ሊጉ ካደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 19ኙን በድል ተወጥቷል። ዓመቱ ትላንት ሲጠናቀቅ 102 ጎል ከመረብ አሳርፏል። በአንፃሩ ቸልሲ የሊጉን ክብር ባለፈው የጨዋታ ዘመን ማግኘቱ አይዘነጋም። ነገር ግን የአንቶንዮ ኮንቲ ቡድን ማሽቆልቆል ቀንቶታል። 

የቶትንሀሙ ሀሪ ኬን በ2017፤ 39 ጎሎችን ከመረብ በማሳርፍ አመቱን በስኬት የጨረሰ ተጫዋች ሆንዋል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን 21 ጨዋታዎቸን ያደረገው የእንግሊዝ የፕሪመየር ሊግ በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ 6 አሰልጣኞች በውጤት ማጣት ሳቢያ አሰናብቶ ነው አመቱን የጨረሰው። እረፍት የማያውቀው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ፣ እሁድ አና ዛሬም በአዲሱ አመት በመካሄድ ላይ ነው።  

በአውስትራልያ እና በቻይና እየተካሄደ ያለውን የሜዳ ቴኒስ ውድድር እንዲሁም ዛሬ የተከፈተውን የተጫዋች ዝውውር አካተናል። 

እግር ኳስ 
እረፍት የማያውቀው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የቅዳሜ ጨዋታዎች በርካታ ጎል በማስቆጠር ቸልሲን የተጠጋው የለም። ቸልሲ አመቱን ያጠቃለለው በጎል ተንበሽብሾ ነበር። ቅዳሜ ዕለት ባደረገው የፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ጨዋታው ስቶክ ሲቲን 5 ለምንም አሸንፏል። ፕሪምየር ሊጉን ማንችስተር ሲቲ በ 59 ነጥብ ሲመራ ቸልሲ በ45 ነጥብ ይከተላል። ማንችስተር ዩናይትድ በ44 ነጥብ 3 ሲሆን ሊቨርፑል 41 ነጥብ 4 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዌስት ሀም፣ ዌስት ብሮም እና ሰዋንሲ እንደቅደም ተካተላቸው በወራጅ ቀጠና የተቀመጡ ቡድኖች በመሆን አዲሱን አመት ጀምረዋል።

Benevento Calcio vs US Sassuolo - Serie A
ምስል picture-alliance/Zumapress/NurPhoto/P. Manzo

የጣልያኑ ሴሪ አ 
19 ጨዋታዎችን ያስተናገደው የሴሪ አ ናፖሊ በ48 ነጥብ ሲመራ በአንድ ነጥብ የተበለጠው ጁቬንትስ በ47 ነጥብ ይከተላል። ኢንተር ሚላን በ41 ነጥብ፣ ሮማ በ39 ነጥብ 3ኛ እና 4 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። 

ተጫዋች ቅጣት 

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ አሽሊ ያንግ ባልተገባ ሀይለኛ ግጭት ጥፋት በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህብረሰብ ቅጣት ተበይኖብታል።

የተጫዋች ዝውውር 

ምንም እንኳን ክለቦች የድርድር እና የስምምነት ሳቸኤን አስቀድመው ቢጀምሩም የተጫዋች ዝውውር መስኮት ዛሬ ተከፍቷዋል። ሪያል ማድሪድ 120 ሚልየን ፓውንድ ለቸልሲው ኤድን ሀዛርድ ዝውውር ለመክፈል እንደተዘጋጀ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል። 

የሜዳ ቴኒስ

ሆፕማን ካፕ 30 ወይም 2018 ማስት ርካርድ ሆፕ ማን ካፕ የሚል መጠሪያ በተሰጠው እና በአውስትራልያ ፐርዝ በሚካሄደው የሚዳ ቴኒስ ውድድር 8 ሀገሮች ተካፋይ ሲሆኑ ቅዳሜ በወንዶች ካርን ሀቸኖቨ በአሜሪካዊው ጃክ ሶክ 2ለ1 ተረትተዋል።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ