የስፖርት ጥንቅር፤ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም
ሰኞ፣ መጋቢት 4 2015ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች በተሳተፉባቸዉ እና በሳምንቱ መጨረሻ በተከናወኑ የሜዳ ላይ ዉድድሮች አስደናቂ ዉጤቶችን አስመዝግበዋል። ትናንት እሁድ በሰሜናዊ ስፔን ላሬዶ ከተማ ዉስጥ በተካሄደ የ10 ኪሎሜትር የዓለማቀፍ የሩጫ ዉድድር ኢትዮጵያዊዉ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 26 ደቂቃ ከ 33 ሰከንድ በመግባት ድልን ተጎናፅፏል። አትሌት በሪሁ የገባበት የዉድድር ሰዓት በዓለማችን ሁለተኛዉ ፈጣን ሰዓት ሆኖም ተመዝግቧል። አትሌት በሪሁ ያስመዘገበዉ የአሸናፊነት ሰዓት የኢትዮጵያን የሪከርድ በ 23 ሰከንድ ያሻሻለበት እንደሆነም ነዉ የተነገረዉ። አትሌት አልማዝ አያና እና አትሌት ንብረት መላክ፤ በሊዝበኑ ግማሽ ማራቶት ዉድድር አሸናፊ ሆነዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባህርዳር ላይ የግማሽ ማራቶን ዉድድር ተካሂዷል። በዛሬዉ የስፖርት ዝግጅታችን ይህን እና የጀርመን ቡንደስሊጋ ብሎም የኢንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ ዉድድሮችን እና ዉጤቶቻቸዉን አቀናብረን ይዘናል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ