1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብስክሌት አገልግሎት መዳከምና ዳግም ትንሣኤ በባሕር ዳር

ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2014

ባሕር ዳር ላይ ከዚህ ቀደም የነበረው ቀርቶ ለብስክሌት ስፖርት እና የመጓጓዣ አገልግሎት መዳከም የብስክሌት ስፖርቱ ክልብ አለመታቀፉ እና ሌሎች የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪ አማራጮች በከተማው በመበራከታቸው ምክንያት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።

https://p.dw.com/p/47QqW
Äthiopien I Fahrradkultur in Bahrdar
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ብስክሌት እና ባሕር ዳር

በባሕር ዳር ከተማ እየተዳከመ የመጣውን የብስክሌት ስፖርት እና የመጓጓዣ አገልግሎት እንደገና ለማስጀመር የሚያስችል የብስክሌት ፌስቲቫል እና ውድድር በባሕር ዳር ተካሂዷል። ለብስክሌት ስፖርት እና የመጓጓዣ አገልግሎት መዳከም የብስክሌት ስፖርቱ ክልብ አለመታቀፉ እና ሌሎች የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪ አማራጮች በከተማው መበራከታቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።

አሁን ስፖርቱንም ሆነ የብስክሌት መጓጓዣን ወደከተማዋ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ያደነቁት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ዶ/ር ዘመኑ ተሸመ መንግሥትም ኅብረተሰቡ ከብስክሌት እየራቀ የመጣው የታክሲዎች እና ሌሎች የመጓጓዣ አገልግሎቶች መበራከታቸውን ተከትሎ ተጠቃሚው አደጋን ከመፍራቱ ጋር እንደሚያያዝ ይናገራሉ። ባለፈው እሁድ በተዘጋጀው የብስክሌት ፌስቲቫል ላይ የ30 ኪሎ ሜትር የወንዶችና የ20 ኪሎ ሜትር የሴቶች የብስክሌት ውድድሮች ተካሂደዋል፣ ለአሸናፊዎቹም የምስክር ወረቀት ተስጥቷል።
ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ