በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ
ሐሙስ፣ ኅዳር 14 2010ማስታወቂያ
የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ከዚህ ቀደም ጥሎ የነበረው የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲራዘም ማድረጉ አግባብ አይደለም ተባለ። ስለ ማዕቀቡ ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ውሳኔው ተጨባጭ ማስረጃን ያገናዘበ አይደለም ብለዋል።ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢውን መልክዐ ምድራዊ ፖለቲካ ያጠኑት ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ በሰጡት አስተያየት የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ራሳቸው ውሳኔውን ምን ያህል ያከብሩታል የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ዝርዝሩን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ