ስፖርት
ሰኞ፣ ነሐሴ 9 2008ማስታወቂያ
አልማዝ አያና ርቀቱንን 29ደቂቃ ከ17 ነጥብ 4 5 በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝግባለች። በ15 ነጥብ ከ08 ስከንድ ተቀድማ ኬንያዊትዋ ቪቪያን ቺሪዮት ሁለተኛ ስትሆን 25ነጥብ ከ11 ሰከንድ ልዩነት ጥሩንሽ ዲባባ ፈጣን ሰዓት በመሮጥ የነሐስ ሜዳልያውን አግኝታለች።
በአጭር ርቀት በተደረገው ውድድር በ100 ሚትር ለሦስተኛግዜሁሴን ቦልት አሸናፊ ሆንዋል።የ 29 ዓመቱ ጃማይካዊ9 ነጥብ ከ81 ሰከንድ በመጨረስ ጀስቲንን በመቅደም ነዉየወርቅ ሜዳልያውን የወሰደዉ።የደቡብ አፍሪካው ዋዲ ቫን ኒክሪክ በ400 ሜትር ርቀት ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን ሰብሯል።ለ17 ዓመት በማይክል ጆንሰን ተይዞ የነበረውን ርቅት የሰበረው በ43ነጥብ ከ03 ሰከንድ በመጨረስ ነው ። ይህንና ሌሎች ያለፈዉ ሳምንት ዝርዝር ስፖርታዊ ክንዉኖች ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ