የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔ በኤርትራ ላይ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 4 2009ማስታወቂያ
የኤርትራ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ይፈፅማል የሚባለዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተለይም የዘፈቀደ እስራት እንዲያቆም የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ጠየቀ።ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ የሚሰየመዉ የምክር ቤቱ ሥብሰባ እንዳለዉ ለረጅም ጊዜ የታሰሩት ጋዜጠኛ ዳዊት ኢሳቅ፤ፓትሪያርክ አንቶኒዮስ እና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቋልም።የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ከኤርትራ መንግሥት ጋር ያለዉን ግንኙነት ለመቀጠል መወሰኑንም የሕብረቱ ምክር ቤት ተቃዉሞታል። የብራስልሱ ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ