የአውሮጳ ህብረት የፓርላማ አባላት ምርጫ እና ከፊቱ የተጋረጠው ፈተና
ዓርብ፣ ግንቦት 30 2016አራት ቀናት የሚዘልቀው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ
የአውሮጳ ህብረት 27 አባል አገሮች ከትናንት ጀምሮ እስከ ነገና ከነገ ወዲያ ዕሁድ ድረስ የአውሮፓ ፓርላማ ወኪሎቻቸውን እየመረጡ ነው። ትናንት ኔዘርላንድስ፤ ዛሬ አየርላንድና ቼክ ሪፑብሊክ የመረጡ ሲሆን፤ ነገና ከነገ ውዲያም በቀሩት የህብረቱ አገሮች ምርጫው ይቀጥላል። ከጠቅላላው የህብረቱ 450 ሚሊዮን ህዝብ 370 ሚሊዮኖች መምረጥ የሚችሉና የተመዘገቡ ሲሆኑ፤ ዘንድሮ የመራጩ ህዝብ ተሳትፎ ከመቺውም ግዜ የላቀ እንደሚሆን ተገምቷል ።። ከ27ቱ አባል አገሮች የሚመረጡ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ቁጥር 720 ሲሆን፤ ከየአገሮቹ የሚመረጡት የፓርላማ አባላት ብዛት ግን በያገሮቹ የህዝብ ብዛት መጠን የተደለደለ ነው።
የምርጫው ሂደትና በፓርላማው የፖለቲካ ቡድኖች
የፓርላማ አባሎቹ በየአገሮቻቸው በተለያዩ ፓርቲዎች ወይም በግል ተወክለው የሚወዳደሩና የሚመረጡ ቢሆንም፤ ብዙዎቹ በፓርላማው፤ ባውሮፓ ደረጃ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ተካተው ወይም ተደራጅተው ነው የሚሰሩት። የመሀል ቀኙ የክርስቲያን ዴሞክራቶት ፓርቲዎች ስብስብ EPP)፤ የመሀል ግራው የሶሻልና ዴሞክራቶች ስብስብ (S & D)፤ የሊበራሎቹ ቡድን፤ ያረንጉዴዎቹና የግራ ኃይሎች ስብስቦች፤ የወግ አጥባቂዎቹና የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ስብስቦች ዋና ዋናዎቹ የፓርላማው የፖለቲካ ስብስቦች ወይም ቡድኖች ናቸው።
የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ አዲስ የስደተኞች ሕግ አፀደቀ
የዝነድሮው ምርጫ ልዩ የሆነበት
የዘንድሮው ምርጫ ህብረቱ በዩክሬን ምክኒያት በተዘዋዋሪም ቢሆን ከሩሲያ ጋር በጦርነት ውስጥ ባለበት፤ የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት የህብረቱ አይነተኛ ፈተና በሆኑበት፤ የፈላስያንና ስደተኖች ጉዳይ በሰፊው እየተወሳ ባለበትና ከሁሉም በላይ ግን ከዚህ ቀደም ታይቶ ባልታወቀ ሁኒታ በሁሉም የህብረቱ አገሮች በሚባል ደረጃ እራሱን ያውሮፓ ህብረትንም ከጥያቄ ውስጥ የሚያገቡ የቀኝ አክራሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባንሰራሩበትና ባንዳንዶችም መንግስት እስከመሆን በደረሱበት ወቅት የተካሄደና እየተካሄደ ያለ በመሆኑ ልዩ፤ አጓጊና አሳሳቢም ሁኗል ።
የአክራሪ ብሄረተኞች ድጋፍ ለምን ጭመረ?
የአክራሪ ብሄረተኖችና የህዝበኛ ፓርቲዎች ማደግና ምክኒያቶች በርካታ ቢሆኑም በለንደን እስኩል ኦፍ ኢኮኖሚስ ፕሮፈሰር ስቲፋኒ ሪካርድ እንደሚሉት ዋናው ምክኒያት ግን ኢኮኖሚው ነው፡ “ ዋናው ምክኒያት የሚሆነው የኢኮኖሚ ዋስትና ማጣት ነው። መራጩ ህዝብ እያደገ የሚሄደው የዋጋ መናርና የኑሮ ውድነት ያሳስበዋል” በማለት ብሄረተኛና ህዝበኛ ፓርቲዎች ይህን ችግር ድጋፍ ለማገኘት እንደሚጠቀሙበትም አመላክተዋል።
ትኩረት የሳበው የአውሮጳ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
የምርጫ ዘመቻ አጀንዳዎች
የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ፤የአየር ንብረት ለውጥ፤ የስደተኖችና ፈላስያን ጉዳይ፤ የዩክሬኑ ጦርነትና የአውሮፓ ደህንነት ጉዳዮች ዋናዎቹ የልዩነቶችና የምርጫ ዘመቻ አጀንዳዎች ናቸው። በዚህ ምርጫ ውጤት የሚመስረተው የፓርላማ አይነት፤ ህብረቱ በነዚህ አጀንዳዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃና የሚከተለውን ፓሊሲ ይወስነዋል።
የአዲሱ ፓርማ የመጀመሪያ ስራና የሚጠበቁ ተግዳሮቶች
የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ የኮሚሽኑን ፕሬዝድናት መምረጥ ሲሆን፤ ይህም በዲሱ ፓርላማ አዲስ የሀይል አሰላለፍ የሚወሰን ይሆናል። ትልቁ ፓርቲ ይሆናል ተብሎ የተገመተው የመሀል ቀኙ የአውሮፓ ህቦች ፓርቲ (ኢፒፒ)፤ ወይዘሮ ቮንዴር ሌየንን በቀጣይም የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በዕጩነት ያቀረበ ሲሆን ፤ ይህ ግን ነባር አጋሮች ሆነው ከቆዩት የሶሻሊስቶቹና ሊበራሎቹ የምርጫ ውጤት ጋርም የሚያያዝ ነው። በብዙዎች እንደሚገመተው የወግ አጥባዊቹና የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ሁለተኛ ትልቆቹ ፓርቲዎች ከሆኑ፤ ወይዘሮ ቮንዴር ለየን የነሱን ድጋፍ ለማግኘት ከነሱ ጋር በዋናዎቹ የህብረቱ መርሆች ጭምር እንዲደራደሩ ሊገደዱ ይችላሉ ነው የሚባለው። ይህ ከሆነ ደግሞ ያውሮፓ ህብረት ከበርካታ አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ቀኝ ያደላ መሆኑ የማቀር ነው፤ እንደ ፖለቲካ ታዛቢዎች አስተየየት።
የአውሮጳ ሕብረት በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ
ያዲሱ ፓርላማ ተጠባቂ ችግሮች
የአክራሪና ህዝበኛ ፓርቲዎች ተወካዮች በፓርላማው በብዛት ከገቡ በህብረቱ ፖሊስዎችና የስራ ሂደት ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ መሆኑን በፓርላማው የአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ (ኢፒፒ) ቡድን ፕሬዝዳንት ሚስተር ማንፍሬድ ዌበር ሳይቀር ይናገራሉ፤ “ የመጀመሪያው ነገር እነዚህ ወገኖች ለችግሮች በሚቀርቡ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ አይስማሙም። ብሄረተኖች መራደርና ሰቶ መቀበል አያውቁም። ሁለተኛ፤ የራሳቸውን ምርት የሚያስቀድሙና የሌላውን የሚከለክሉ ነው የሚሆኑት፡፤ ለምሳሌ ወይዘሮ ለፔን ፕሬዝዳንት ቢሆኑ፤ በፈረንሳይ የፈረንሳይ የምርት ውጤቶች ብቻ ለገበያ እንዲቀርቡ ነው የሚጠይቁት፤ ሼንገንም ችግር ውስጥ ሊገብ ይችላል፤ ለዩዩኪረን በሚሰጠው ድጋፍ ላይም ጥያቄ ሊነሳ ይችላል በማለት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ይዘርዝራሉ ።
የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ
ባጠቃላይም የዘንድሮው ምርጫ ውጤት የአውሮፓ ህብረት ወደ ቀኝ እንዲያደላ የሚያደርግና ይህም በህብረቱና አለምቀፍ ጉድዮች ጭምር የፖሊሲ ለወጦች ማስክተሉ የማይቀር እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሁሉንም ግን በመጪው ሰኞ ይፋ በሚሆነው የምርጫ ውጤት ለማየት ሁሉም በጉጉትና በጭንቀት ጭምር በመጠባበቅ ላይ ነው።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ