1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ ከያኒያን የጋራ ትርዒት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2011

የትርዒቱ አዘጋጆች እና አቅራቢዎች እንዳሉት የሁለቱ ሐገራት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዓሉን በጋራ ማክበራቸዉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ሕዝብ-ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ባለፈዉ መስከረም የተከፈቱ የዛላንበሳ እና የራማ የድንበር ኬላዎች ግን የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያዉያን ተጓዞችን የይለፍ ማስረጃ በመጠየቁ ለተጓዦች እንደተዘጉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3ArpA
Äthiopien | Äthiopier und Eriträer feiern Neujahr 2019 in Mekelle
ምስል M. Haileselassie 

የኢትዮ-ኤርትራ ከያኒያን የጋራ ትርዒት 

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የጎርጎሪያኑን የዘመን መለወጫ በዓል መቀሌ-ትግራይ ዉስጥ በጋራ አከበሩ።በ2019 ዋዜማ ትናንት በተዘጋጀዉ በዓል የሁለቱ ሐገራት ድምፃዉያን የሙዚቃ ድግስ፣ የሞዴል ባለሙያዎች ደግሞ የተለያዩ የጥበብ ትርዒት አሳይተዋል። የትርዒቱ አዘጋጆች እና አቅራቢዎች እንዳሉት የሁለቱ ሐገራት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዓሉን በጋራ ማክበራቸዉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ሕዝብ-ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ባለፈዉ መስከረም የተከፈቱ ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙ የዛላንበሳ እና የራማ የድንበር ኬላዎች ግን የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያዉያን ተጓዞችን የይለፍ ማስረጃ በመጠየቁ ለተጓዦች እንደተዘጉ ነዉ። የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ