የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ኮንፍረንስ በአዲግራት
ሐሙስ፣ ጥር 16 2011ማስታወቂያ
በዛሬው ኮንፈረንስ የመነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር የሆኑት አቶ አለሙ አስፋው የተጀመረውን ግንኙነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ አጋጣሚዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ምሁሩ ከጠቀሷቸው ፈተናዎች መካከል የሀገራቱ መሪዎች ባህርያት ይገኝበታል፡፡ እንደ ምሁሩ ገለፃ በተለይም በኤርትራ ወገን የፕሬዝዳንቱ የግል ባህሪ በሀገራቱ ግንኙነት ላይ ጫና የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
ሌላው የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንሱ ተሳታፊ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህሩና የዓረና ሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ በሁለቱ ሀገር ህዝቦች መካከል 'ምንም ጠብ የለም' ብለዋል፡፡ በመሪዎቹ በኩል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በማድነቅ፡ በቀጣይነት የስምምነቱ ይዞታ ለህዝብ ይፋ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከኤርትራውያን ወገን የሆኑት "የሲቪል ማሕበረሰብ ኤርትራ" ተወካይ አቶ ዳዊት ይብራህ ለሁለቱ ሀገራት ዘላቂ ሰላም የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሚሊዮን ሃይለስላሴ
ተስፋለም ወልደየስ
እሸቴ በቀለ