የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር መዘጋት
ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያና ኤርትራን በየብስ የሚያገናኙ መስመሮች ተራ በተራ ግን በሙሉ ተዘግተዋል።አሁን የተዘጉት መስመሮች ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ ሲከፈቱ፣ ሁለቱ ሐገራት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ዜጋቸዉን የፈጀዉን ጦርነትና ጠብ ለማስወገድ ያደረጉት ሥምምነት አብነት ተደርጎ ነበር።ሁሉንም መስመሮች የዘጋዉ የኤርትራ መንግስት ነዉ።ይሁንና የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት መስመሮቹ ሥለተዘጉበት ምክንያት እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።ሥለጉዳዩ እናዉቃለን የሚሉ ወገኖች እና የፖለቲካ ተንታኞች ግን የተለያዩ ምክንያቶችን ይሰጣሉ።
ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋአለም ወልደየስ