የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት እንዲሻሻል መጠየቁ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2006ማስታወቂያ
ጦርነትም ሰላም በሌለበት ሁኔታ ሁለተኛውን አሥርት ዓመት በማጋመስ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን እንዲያሻሽሉ ተጠየቁ ። ቻተም ሃውስ የተባተለው የለንደኑ የጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ ጄሰን ሞስሊ በቅርቡ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በአዲስ መልክ ለማስተካከል ሙከራ እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበዋል ። ግንኙነቱ መሻሻሉ ለሃገራቱ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ያስታወቁት ሞስሊ ይህን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያና ኤርትራ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ችግራቸውን መፍታት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ። ሞስሊን ያነጋገረቸው የለንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።
ሃና ደምሴ
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ