የኢትዮጵያ እና የፀጥታው ምክር ቤት
ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2009ማስታወቂያ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሃገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በሶሪያ የኬሚካል ጥቃት ላይ ምርመራ እንዲኪያሄድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምጸ-ተአቅቦ አድርጋለች። በመንግሥታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ ብሩክ መኮንን ድምጸ-ተአቅቦው ጥቃቱን ከማውገዝ ጋር ተያይዞ የተሰጠ ድምጽ ነው ብለዋል። ቻይና ድምጸ-ተአቅቦ በማድረጓ ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ለቻይና ድጋፏን ለማሳየት ነው የሚለውንም ሐሳብ ተቃውመውታል። አንድ የዓለም አቀፍ ምሁር ደግሞ ተከሰተ የተባለው የኬሚካል ጥቃት ሙሉ ለሙሉ በገለልተኛ አካል ያልተረጋገጠ በመኾኑ ኢትዮጵያ የተሻለ አቋም ይዛለች ብለዋል።
መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ