የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሳተላይት ከቻይና መጠቀች
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2012አብዛኛው ወጪ ከቻይና መንግሥት ፈሰስ የተደረገባት የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሳተላይት ሰሜን ምሥራቅ ቻይና ሻንሺ አውራጃ ውስጥ ከሚገኘው የሳተላይት ማስወንጨፊያ እንድትመጥቅ ተደረገ። በኢትዮጵያውያን እና ቻይናውያን መሐንዲሶች እንደተሠራች የተነገረላት 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ይኽች ሳተላይት በእንግሊዝኛ ምኅጻር (ETRSS1) እንደምትሰኝ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ወደ ምኅዋር ስትመጥቅ ይኽ የመጀመሪያው ነው።
ሳተላይቷ፦ የኢትዮጵያን ግብርና ለማዘመን፤ «በድንበር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎችን፤ እና ትላልቅ ፕሮጀክቶን ለመከታተል» ብሎም የአየር ጸባይን በመመልከት መረጃ ለመሰብሰብ እንደምታገለግል ተጠቅሷል። የሳተላይቷ መኖር ከዚህ ቀደም ምስሎችን ከሌሎች ሃገራት ለመግዛት የሚወጣውን ወጪም ማስቀረት ያስቻላል ተብሏል።
ሳተላይቷ ከቻይና እንድትመጥቅ ስትደረግ በሀገር ቤትም የተለያዩ ዝግጅቶች ተከናውነዋል። በእንጦጦ የሳተላይት መልእክት መቀበያ ማዕከል በተከናወነው ስነ ሥርዓት ምክትል ጠቅላይ ሚንሥትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ በርካታ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በስነ ሥርአቱ ላይ ተገኝተዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከስፍራው በመገኘት ያሰናዳውን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ