የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያንን የጋራ መርሃ ግብር
ሰኞ፣ ነሐሴ 28 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት በመካከላቸው የነበረውን አለመግባባት እና ወደ ጦርነት ሊያመራ የሚችለውን ፍጥጫ በማስወገድ ሰላም ለማውረድ በመቻላቸው በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን እና ኤርትራውያን በልዩ ልዩ የጋራ መርሀ ግብሮች ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ቤልጂግ የሚኖሩ የሁለቱ ሀገራት ተወላጆችም ባለፈው ቅዳሙ በኮርትሬክት ከተማ ባዘጋጁት የጋራ መርሃ ግብር ላይ የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጎለብት እና አንድ በሆኑት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ግንኙነት ይበልጥ እንዲዲሰፋ በማሳሰብ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ