1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ 28ኛ ዓመት የነፃነት በዓል

ዓርብ፣ ግንቦት 16 2011

የኤርትራ መንግስት የሚቆጣጠረዉ ቴሌቪን ጣቢያ እንደዘገበዉ በዓሉ የሚከበረዉ «ፅናት፣ በፅናት ለልማት» በሚል ዓብይ መፈክር ነዉ።የዘንድሮዉ በዓል የሚከረበዉ ኢትዮጵያና ኤርትራ 20 ዓመታት ያስቆጠረ ዉጊያ፣ጠብ ዉዝግባቸዉን አስወግደዉ ሠላም ባወረዱ፣ በኤርትራ ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ በተነሳ ማግሥት ነዉ

https://p.dw.com/p/3J2nR
Saudi Arabien Äthiopien und Eritrea schließen Freundschaftsvertrag
ምስል picture-alliance/dpa/SPA

የኤርትራ 28ኛ ዓመት የነፃነት ቀን


ኤርትራዉያን እንደነፃነት ቀን የሚቆጥሩት የቀድሞዉ የኤርትራ ነፃነት ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አስመራን የተቆጣጠረበት ዕለት 28ኛ ዓመት ዛሬ በሐገሪቱ የተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ነዉ።የኤርትራ መንግስት የሚቆጣጠረዉ ቴሌቪን ጣቢያ እንደዘገበዉ በዓሉ የሚከበረዉ «ፅናት፣ በፅናት ለልማት» በሚል ዓብይ መፈክር ነዉ።የዘንድሮዉ በዓል የሚከረበዉ ኢትዮጵያና ኤርትራ 20 ዓመታት ያስቆጠረ ዉጊያ፣ጠብ ዉዝግባቸዉን አስወግደዉ ሠላም ባወረዱ፣ በኤርትራ ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ በተነሳ ማግሥት ነዉ።በዓሉን በማስመልከት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ የተለያዩ ሐገራት ርዕሠነ-ብሔራትና መራሕያነ-መንግስታት ለኤርትራ መሪና መንግስት የደስታ መግለጫ መልዕክት እያስተላለፉ ነዉ።ኤርትራ በይፋ ከኢትዮጵያ የተገነጠለችዉ በ1985 ከተደረገዉ ሕዝበ ዉሳኔ በኋላ ነዉ።ኤርትራዉን እንደነፃነት ቀን የሚያከብሩት ግን የዛሬዉን ቀን ነዉ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋአለም ወልደየስ