1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ ገቡ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 19 2010

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌሕ አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ለእንግዶቹ ጉንጉን አበባ ከአንገታቸው አጥልቀው ተቀብለዋቸዋል።

https://p.dw.com/p/30Ixe
Äthiopien Addis Abeba Abiy Ahmed begrüßt Delegation aus Eritrea
ምስል Prime Minister Office/Fitsum Arega

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌሕ የተመራ የኤርትራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ እና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኦስማን ሳሌሕ ጉንጉን አበባ ከአንገታቸው አጥልቀው ተቀብለዋቸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነሕ ገበየሁ፣ አቶ አሕመድ ሽዴ፣ ዶክተር አርከበ እቁባይ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት ለሁለት አስርት አመታት ገደማ በሁለቱ አገራት መካከል ሰፍኖ የቆየው ውጥረት ማብቂያ እንደሆነ የጠቅላይ ምኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ጽፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የኤርትራ ልዑካን ቡድን ጉብኝት ለተሻለ መፃኢ ጊዜ መሠረት እንደሚጥል ተስፋ እንዳላቸው አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል።

Äthiopien Addis Abeba Abiy Ahmed begrüßt Delegation aus Eritrea
ምስል Prime Minister Office/Fitsum Arega

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ