የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ ስበሰባ በኔዘርላንድስ ታገደ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2009ማስታወቂያ
ከኤርትራ መንግሥት ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ለፍትኅ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የኤርትራ ወጣቶች ዓመታዊ ጉባኤ ኔዘርላንድስ ውስጥ እንዳይካሄድ ታገደ። በጉባኤው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ነበር። ኔዘርላንድስ የኤርትራ ወጣቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ለሚመጣ ለማንኛም የኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣን አንዳችም ድጋፍ እንደማታደርግ ቀደም ሲል ገልጻለች። አቶ የማነ ገብረ አብ ኔዘርላንድስን መጎብኘታቸው «የሚያሳፍር» ነው ሲልም የሀገሪቱ ካቢኔ ተናግሮ ነበር። ጉባኤው የታገደው ፌልድሆቨንስ በተባለችው ከተማ ውስጥ ትናንት በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ከተከሰተ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናቱ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ደኅንነት እና ጸጥታው በበቂ ኹኔታ አስተማማኝ ሊኾን ስለማይችል ጉባኤው እንደታገደ መግለፃቸው ተዘግቧል። የብራስልሱ ወኪላችን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ