የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ይዞታ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2011ማስታወቂያ
ኤርትራ በተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠቅላላ ጉባኤ አባል መሆኗም ጥያቄ እያስነሳ ነው። በዘንድሮው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 41ኛ ጉባኤ የኤርትራ ጉዳይ ትልኩረት እንደሚደረግበት ይጠበቃል። በሌላ በኩል ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ማምሻ ወዲህ ኢትዮጵያ ዳግም ስጋት እና ማስጠንቀቂያን ያዘሉ የፖለቲካ ምሁራን ትንታኔዎችን ባካተቱ ዘገባዎች ተደጋግማ ስትነሳ ነው የሰነበተችው። የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንን እና የፖለቲካ ቀውስ ተከታታይ ተቋማትን ትኩረት ዳግም የሳበችው ሀገር ላለፉት 14 ወራት ገደማ የለውጥ ተስፋዋ እና ፖለቲካዊ ቀውስን ለመፍታት ሰላምን በማስፈን ረገድ የአዲስ ፈር ቀዳጅነትዋ ተወርቶ አላባራም ነበር። ተስፋው ቀቢጸ ተስፋ የሆነባቸው እንዳሉ ሁሉ ፤ ክስተቱ በለውጥ ሂደት የሚያጋጥም እንከን መሆኑን በመግለፅ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ጉዞ እንዳይጨናገፍ ስስታቸውን በጥንቃቄ የሚያስተጋቡም በርካቶች ናቸው። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ የተለያዩ ጋዜጦችን ሲያገላብጥ ይህን ያስተዋለ መሆኑን ያካተተበት የዕለቱ የጋዜጦች አምድ ጥንቅር ቀጥሎ ይቀርባል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ