1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ግልፅ ደብዳቤ

ሰኞ፣ ሰኔ 18 2010

ዋና መሥርያ ቤቱን በብሪታንያ ያደረገዉ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በመላዉ ኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የጀመሩትን ፈጣን የለዉጥ አቅጣጫ አደነቀ።

https://p.dw.com/p/30Fti
Karte Eritrea Djibouti DEU
ምስል DW

ለጠ/ም ዐብይ አሕመድ ግልፅ ደብዳቤ


የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ኤልዛቤት ጭሩም ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ በቂ ምክንያት ብዙ ደም ያፋሰሰዉን የኢትዮ- ኤርትራ የድንበር ግጭት ለማብቃት የተወሰነዉ የአልጀርስ ሥምምነት ገቢራዊ ሲደረግ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት በማይጎዳ መልኩ እንዲሆን ሲልም ተማፅኖአል። የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የፃፈዉን ግልፅ ደብዳቤ በተመለከተ የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳዉ ጌታነህ የድርጅቱን ዋና ፀሐፊ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 


ድልነሳ ጌታነህ

አዜብ ታደሰ  
ሸዋዬ ለገሠ