የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት
ሐሙስ፣ መጋቢት 26 2011ማስታወቂያ
አንድ የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ድርጅት የአዉሮጳ ኅብረት በኤርትራ የሚፈፀመዉን የግዳጅ ሥራ በገንዘብ ይደግፋል ሲል ወቀሰ። መቀመጫዉን ኔዘርላንድስ ያደረገዉ ይኸዉ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በሳምንቱ መጀመርያ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ ብራስልስ ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የአዉሮጳ ኅብረት፣ የኤርትራ መንግሥት የግዳጅ ሥራ የሚካሄድባቸውን ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በገንዘብ የሚደግፍ መሆኑን በመግለፅ ርምጃዉ የአዉሮጳ ኅብረትን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች የሚፃረር መሆኑን አስታዉቋል።የኤርትራዉያኑ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የአዉሮጳ ኅብረት እየፈፀመ ያለዉን ይህን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በሕግ እጠይቃለሁም ሲል አስጠንቅቆአል። በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ የተገኙ የሕግ ባለሞያዎች በኤርትራ ይፈፀማል ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፤ በተለይ ብሔራዊ ዉትድናን እና የግዳጅ ሥራ እንዲሁም ሕገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ሁሉ ኅብረቱ ተባባሪ ሆንዋል ሲሉ አጋልጠዋል።
ገበያዉ ንጉሤ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ