የእስራኤልና የሐማስ ጦርነት፤ የመንግስታት ዉዝግብ
ረቡዕ፣ መስከረም 30 2016
እስራኤል፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ አዉሮጳና ጀርመን በአሸባሪነት የፈረጁት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስ ባለፈዉ ቅዳሜ እስራኤል ካጠቃ ወዲሕ የአብዛኛዉ ዓለም ትኩረት በመካከለኛዉ ምሥራቅ ላይ አነጣጥሯል።በሐማስ ጥቃትና በእስራኤል አፀፋ ጥቃት ከሁለቱም ወገኖች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሺሕ በልጧል።የዓለም መንግስታት ጎራ ለይተዉ ተዋጊዎችን ከመደገፍ ባለፍ ሰላማዊ ሰዎችን የሚፈጀዉን ጦርነት ለማስቆም እስካሁን የወሰዱት ሁነኛ ርምጃ የለም።በተለይ ምዕራባዉያን መንግስታት ጭልጥ ብለዉ ለእስራኤል ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠታቸዉን ወይም ለመስጠት ቃል መግባታቸዉ ወትሮም ሠላም የማያዉቀዉን ምድር በከፋ የደም አበላ እንዳጠምቀዉ አስግቷል።
ሀማስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በጋዛ አካባቢ ባሉ መንደሮች ዘልቆ በመግባትና በሙዚቃ ድግስ በታደሙ ወጣቶች ላይ ጭምር ተኩስ በመክፈት ያጠፋው ህይወትና ያደረሰው ጉዳት በእርግጥ ብዙዎችን አስደንግጧል። እስካሁን በጥቃቱ 1200 ሰላዊ ሰዎች ተገድለዋል በርካቶች ቆስለዋል፤ መቶ የሚሆኑ ደግሞ ተወስደዋል ተብሏል ። ወዲያው በእስራኤል በኩል በተጀመረው የአጸፋ እርምጃ ደግሞ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኑዋሪዎች ያሏት ጋዛን የቦንብ ናዳ ያወርድባት ይዟል።። እስካሁን አንድ ሺ የሚሆኑ ሰላምዊ ሰዎች እንደተገደሉና በሺ የሚቆጠሩ እንደቆሰሉ ሁለት መቶ ሺ የሚሆኑ መጠለያ አልባ እንደሆኑ የመንግስታቱ ድርጅት አስታውቋል።፡ ዘመቻው በምድርም ይቀጥላል ተብሏል፤ ሃማስም አሁንም መተኮሱን ያላቆመ ሲሆን፤ በጋዛ እየዘነበ ያለው ቦንብ ካልቆመ፤ የያዛቸውን የአሜርካ፣ ካናዳና ሌሎች አገሮች ዜጎች የሚገኙባቸውን እስራኤላውያን አንድ ባንድ እንደሚገድል አስታውቋል።
ይህን ጭክኔ የተሞላበት ትይንት አሜሪካና ምራባውያን አውግዘው፤ ሀማስን ለይተው ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፤ ከእስራኤል ጎን የሚቆሙ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ሩሲያ በበኩሏ ባወጣቻቸው መግለጫዎች ለሁለቱ ህዝቦች ዝንተአለም በጦርነትና ግጭት መኖር ምክኒያቱ የምራባውያን የተዛባና ኢፍትሀዊ ፖሊስ ነው በማለት በተለይ አሜሪካንን ተጠያቂ አድርጋለች። ቻይና፤ ሁለቱም ወገኖች ግጭት ጦርነቱን አቁመው ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሰላም እንዲፈጥሩ ነው ጥሪ ያቀረበችው። ፕሬዝድንት ጆ ባይደን ግን፤ አሜሪካ ምንግዜም ቢሆን ከኢስራኤል ጎን የምትቆም መሆኗን በግልጽ ቋንቋ ነው የገለጹ፤ “ አሜሪካ ከስስሬል ጎን ትቆማለች። ለእስራኤል ጀርባችንን አንሰጥም። ኢስራኤል እራሷን ለመከላከል በምታክሂደው ዘመቻ የምንስጠውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን” በማለት ለአሜርካ፤ የስስራኤል ጉዳይ ከሁሉ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አመላክተዋል። የብርታኒያው ጠቅላይ ሚንስተር ሚስተር ሪሺ ሱናክም እንደዚሁ ሀማስን ለይተው ተጠያቂ በማድረግ ብርታኒያም ከእስራኤል ጎን የምትቆም መሆኑን ነው ያስትወቁት። “ ህማስና ሀማስን የሚደግፉ ወገኖች ለዚህ የሸብሪ ድርጊትና ግድያ ተጠይቂዎች ናቸው” በማለት አሸባሪዎችን ለማስወገድ የሚደረገውን ዘመቻ አገራቸው የምትደግፍ መሆኑን ግልጽ አድርገዋል።
የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱም ቀድሞውንም በአሸባሪነት የፈረጁትን ህማስን ዓውግዘው፤ እስራኤል ደህንነቷን ለማስጠበቅ ይረዳል የምትለውን እርምጃ የመውሰድ መብት ያላት መሆኑን እውቅና ሰተዋል። ሆኖም ግን የሚካሄዱ ዘመቻዎችና ጦርነቶች አለማቀፍ ህግን ያከበሩ መሆን እንዳለባቸውና ሰላማዊ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑም ጥሪም አስተላልፈዋል።፡የአውሮፓው ኮሚሽን በእስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለፍልስጤም አስተድደር የሚስጠውን እርዳታ ሊያቆም ነው ተብሎ የነበር ቢሆንም፤ የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት በዚህ ጉዳይ ላይ ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ ግን፤ የአውሮፓ ህብረት ከፍልስጤም አስተዳደር ጋር የሚያደርገው ትብብር እንዲቀጥልና የልማት እርድታውም እንዳይቋረጥ የተስማሙ መሆኑን የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ህላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ቦርየል ትናንት ማምሻውን በስጠቱት መግለጫ አስታውቀዋል ።
በሃማስ፣ የፍልስጤም አስተድደርና በፍልስጤም ህዝብ መክከል ልዩነት ያለ መሆኑን ያወሱት ቦርየል፤ “ ከፍልስጤም አስተዳደር ጋር በጋራ እንሰራለን እንተባበራለን። ሁሉም የፍልስጤም ህዝብ አሸባሪ አይደለም። በመሆኑም ሁሉንም በጅምላ መፈረጅና መቅጣት ተገቢም ትክክልም አይሆንም” በማለት ሚኒስትሮቹ ከፍልስጤም አስተዳደር ጋር ያለው ትብብር እንዲቀጥልና ክፍያውም እንዳይስተጉጎል የወሰኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሀማስ እስራኤል ጦርነት ነባሩንና ያልተፈታውን የፍልስጠኤም እስራኤል ችግር ወደፊት በማምጣትየመከክለኛውን ምስራቅ የግጭት ቀጠና እንዳይደረገው ያሰጋ ሲሆን፤ ባንጻሩ የዩክሬንን ጦርነት ትኩረት ሊቀንሰውና በሩሲያ ላይ የሚደረገውን ጫናም ሊያበርደው ይችል ይሆናል የሚሉ ድምጾችም መሰማት ጀምረዋል።
ገበያው ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ