1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋሊያዎቹ 2ኛ ግጥሚያ በካሜሩን

ረቡዕ፣ ጥር 4 2014

33ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የእግር ኳስ ላይ ዘንድሮ ተሳታፊ የኾነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከአዘጋጅ ሀገሯ ካሜሩን ጋር ሁለተኛ ግጥሚያውን ያከናውናል። ዋሊያዎቹ ነገ ከካሜሩን ጋር በሚያደርጉት ግጥሚያ ፍጥነት እና ጉልበት የታከለበት አጨዋወት ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል።

https://p.dw.com/p/45RNi
Fußball Africa Cup of Nations | Äthiopien v Kap Verde
ምስል THAIER AL-SUDANI/REUTERS

የዋሊያዎቹ 2ኛ ግጥሚያ በካሜሩን

33ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የእግር ኳስ ላይ ዘንድሮ ተሳታፊ የኾነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከአዘጋጅ ሀገሯ ካሜሩን ጋር ሁለተኛ ግጥሚያውን ያከናውናል። ዋሊያዎቹ ባለፈው እሁድ ከኬፕ ቬርዴ ጋር ባደረጉት የመጀመሪያ ግጥሚያ 1 ለ0 ተሸንፈዋል። ጨዋታው በተጀመረ 8ኛው ደቂቃ ላይ በተከላካይ በተፈጸመ ጥፋት ያሬድ ባየህ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ከ80 ደቂቃ በላይ ቡድኑ በ10 ተጨዋቾች ተወስኖ ለመጫወት ተገድዷል። በካሜሩን አዘጋጅነት ከባለፈው እሁድ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ብርቱ ፉክክር እየተደረገበት ከነገ ጀምሮ የየምድቡ ሁለተኛ ጫወታዎች ይደረጋሉ። በምድብ አንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ጫወታዋን ነገ ከአዘጋጇ ሀገር ካሜሩን ጋር ታደርጋለች። ዋሊያዎቹ ነገ ከካሜሩን ጋር በሚያደርጉት ግጥሚያ ፍጥነት እና ጉልበት የታከለበት አጨዋወት ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል። በብሄራዊ ቡድኑ አጠቃላይ ዝግጅት እና በሚጠበቁ ጉዳዮች ላይ ማንተጋፍቶት ስለሺ የፓሪስ ዘጋቢያችንን ኃይማኖት ጥሩነህን በስልክ አነጋግሯል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ