Tesfalem Waldyes Eragoረቡዕ፣ ኅዳር 5 2011የሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኛው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ በዕለቱ የዜና መጽሄታችን ቀዳሚ ነው። የህግ የበላይነትን አስመልክቶ የትግራይ ክልል ስላወጣው መግለጫ እና እርሱን አስመልክቶ የመቀሌ ነዋሪዎች የሰጧቸውን አስተያየቶች በተከታይነት ይቀርባሉ። የቀድሞ እስረኞች ስለ ሰሞነኛው የባለሥልጣናት እስር ምን ይላሉ? ስንልም የተወሰኑትን አነጋግረናል። የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ዛሬ አንስቷል። ለውሳኔው ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን እንመለከታለን። አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለአንሳንሱቺ የሰጠውን ሽልማት መንጠቁን ገልጿል። በዚህ ላይም የተጠናቀረ ዘገባ አለን።